የአውሮጳ የሕግና የፍትህ ማዕከል (European Centre for law and Justice ) ባለሥልጣናት ዛሬ ከቀትር በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶችን የተመለከተ ገለጻ ተደረገ።
የአውሮጳ የሕግና የፍትህ ማዕከል (European Centre for law and Justice ) ባለሥልጣናት ዛሬ ከቀትር በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶችን የተመለከተ ገለጻ ተደረገ። የአውሮጳ የሕግና የፍትህ ማዕከል ከቀናት በፊት ሽትራስቡርግ ፈረንሳይ በሚገኘው የሕብረቱ ምክር ቤት በጎን በሚካሄድ መድረክ ኢትዮጵያውን ላይ እየተፈጸመ ስላለ ወከባና ጥቃት እንደሚያደምጥ ዐሳውቆ ነበር። በቀጠሮው መሠረትም በዛሬው ዕለት የመድረኩ ዋነኛ ተናጋሪ ልዑል ዶክተር አስፋወሰን አሥራተ፤ በተለይ «በዝምታ የሚፈጸመው የአማራ ስቃይ» በሚል ርዕስ ዝርዝር ገለጻ አድርገዋል። ልዑል ዶክተር አስፋወን አስራተን በማስተዋወቅ የጀመሩት መድረኩን ከጋበዙት የአውሮጳ ምክር ቤት አባላት አንዱ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፦ «ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ አቅጣጫ ብቻ የእርስ በእርስ ጦርነት ብቻ ያለ ይመስለኝ ነበር» ያሉ ሲሆን፤ ከሚደርሷቸው መረጃዎች ግን ጥቃት ግጭቱ በየቦታው መሰራጨቱን መረዳታቸውን ተናግረዋል። ዶክተር አስፋወሰን በበኩላቸው በገለጻቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በሲቪሎች ላይ እየተፈጸመ ነው ያሉትን ጥቃት እና ግድያ መንግሥት ማስቆም አልቻለም ሲሉ ወቅሰዋል። «ብዙ ጊዜ የመንግሥት ሚና ምንድነው እያልኩ እጠይቃለሁ» ያሉት ልጅ ዶክተር አስፋወሰን አስራተ፤ ቅድሚያ የሕዝቡን ደኅንነት ማስከበር የመንግሥት ኃላፊነት እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተዋል። የአፍሪቃ ኅብረትን ጨምሮ...Read More
