በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት አስመልከቶ ለሴናተር ሮይ ዋይደን ገለጻ ተደረገ

የአማራ ማህበር በኦሪገን የስራ አመራርና የቦርድ አባላትን እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የሚወክሉ 12 አባላትን ያካተተ ልዑክ  በአማራ ህዝብና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ በብልጽግናው መንግሰት እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋት ድርጊት ለህዝብ እንደራሴው ሮይ ዋይደን ገለጻ አደረጉ። የተሰጠው መግለጫ በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የጅምላ ጭፍጨፋ፣ ግድያ፣ መፈናቀል፣ ከስራ መሰናበት፣ እገታ፣ ስደት፣ የጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና ፖለቲከኞች ያለ ፍርድ መታሰርን ያካተተ ነው። የመሰብሰብ፣ ሃሳብን በነጻነት የማራመድና የመያዝ መብት በአገዛዙ ስለመገደቡና ይህን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት በሀገሪቱ ህግ መሰረት ለማካሄድ በሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ላይ አማራ በመሆናቸው ብቻ የዚህ መብት ተሳታፊ እንዳይሆኑ አገዛዙ የሚያደርገውን አምባገነናዊ ድርጊት በማስረጃ በማስደገፍ ማብራሪያ ተሰጥቷል። አረመኔው የብልጽግና መንግስት የአማራ ነው ያለውን ባህል፣ እምነትና ታሪክ እንዴት እያጠፋ እንደሆነ በምስል ማስረጃ ተደግፎ ቀርቧል። የባህል መገለጫዎቹ፣ ቤተ እምነቶቹና ታሪካዊ ቅርሶቹ መውደማቸውን፣ በተለይ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከ100 ዓመታት በላይ እድሜ ያላቸውን አብያተ ክርስቲያናት ከእምነቱ ተከታዮቻቸው ጋር መቃጠላቸው ተገልጿል። ከመጋቢት 2015 ዓም በክልሉ አገዛዙ ጦርነት ካወጀ ጊዜ ጀምሮ ከአራት ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች...Read More