በኦሮምያ አርሲ ዞን የደረሰውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

ከኦሪገን አማራ ማህበር የተሰጠ መግለጫ በኦሮምያ አርሲ ዞን በንጹሃን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ከስርዓቱ ገዳይነት ባህሪይው የመነጨ በመሆኑ ሁሉም የሰው ልጆች ሊያወግዙትና ሊታገሉት የሚገባ ጉዳይ ነው። ይህ የዘር ማጥፋት እንቅስቃሴ እንደ በፊቶቹ ጭፍጨፋዎች ሁሉ በራሱ በአገዛዙ የተዘጋጁና የተፈጸሙ መሆናቸውን በቀላሉ መረዳት ይቻላል። ለዚህም ዋነኛ ማስረጃው ያለምንም ማጣራት የአገዛዙ አፈቀላጤ ሃይሉ አዱኛ ወጥቶ “ኦነግ ሸኔ ፈጸመው” ማለቱና በቀጣይ ቀን ደግሞ “ድርጊቱን የሚያጣራ ልዑክ እልካለሁ” ማለቱ፤ እንዲሁም የአገዛዙ የፕሮፖጋንዳ ሚዲያዎች ከድርጊቱ በፊት ሰብስቦ ምርጫውን ለማደናቀፍ በሃይማኖት ተቋማትና በተከታዮቻቸው ላይ ጥቃት ሊፈጸም ስለሚችል ጉዳዩን እንዳትዘግቡ የሚል አቅጣጫ መስጠቱ ድርጊቱ በዕቅድ ስለመፈጸሙ ማረጋገጫዎች ናቸው። ይህ አረመኔ ገዳይ መንግስት ከመጣ ጊዜ አንስቶ ስንት የአማራ ልጆች ታረዱ፣ ከእነነፍሳቸው በቤታቸው ተቆልፎባቸው ተቃጠሉ፣ ስንቶች በህይዎት ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ተጣሉ፣ ስንቶች ቀባሪ አጥተው ለጅብና ለአሞራ ተዳረጉ፣ ስንት አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ፣ ስንት ንብረት ወደመ ተዘረፈ፣ ስንት ህዝብ ያለማውን ቀየ ትቶ በአማራነቱ ተሳደደ? ለዚህ ማን ምን አደረገ? መልሱ ምንም ከማይፈይድ መግለጫ በቀር ምንም ነው። እረኛ ተብለው...Read More