Meeting Reminder Amhara Association of Oregon would like to invite all Amhara community and supporters to attend a virtual meeting on October 3rd 2026 at 8 pm. Miss it not!
ተመድ በኢትዮጵያ በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰው ግድያ አሳስቦኛል አለ በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ሁኔታና የድሮን ጥቃት አሳስቦኛል ሲል የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ አስታወቀ በኢትዮጵያ ፈጽሞ በተለየ ሁኔታ እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ሁኔታና በቅርብ ጊዜ በኢትዮጵያ የተከሰቱት ክስተቶች፣ አዲስ የታጠቁ ቡድኖች ጥምረት መመስረትና ቀጣይነት ያለው የጸጥታ ችግር እንዲሁ በዘፈቀደ የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶችና በንጹሃን ዜጎች ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን አስመልክቶ የሚደርሱ ሪፖርቶች በጣም አሳሳቢ መሆናቸውን በቃለ አቀባዩ በኩል ተገልጿል። በከፍተኛ ውጥረት ወቅት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሁኔታውን የበለጠ ሊያባብሱ ከሚችሉ ድርጊቶች ወይም ንግግሮች እንዲቆጠቡ፤ ችግሮችን በውይይት እንዲፈቱ እናሳስባለን ያለው ሪፖርቱ ወታደራዊ እርምጃ የፖለቲካ ልዩነቶችን ወይም መሰረታዊ ቅሬታዎችን አይፈታም ብሏል። በአማራ፣ በትግራይና በኦሮምያ በመንግስት ወታደሮች በርካታ ንጹሃን ዜጎች በግፍ እየተገደሉ፣ እየተፈናቀሉ ለስደት እየተዳረጉ መሆኑን ላለፉት ሰባት ዓመታት በመገናኛ ብዙሃን ሲዘገብ መቆየቱና የተባበሩት መንግስታት በጉዳዩ ዙሪያ ምንም ትኩረት አለመስጠቱ የሚታወስ ነው።