እንቁጣጣሽ! መልካም አዲስ አመት
እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት አደረሳችሁ! የአማራ ማህበር በኦሪገን ለማህበሩ አባላትና ለመላው ኢትየጵያውያን አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ ይላል። ከአሮጌው ዘመን በመማር ለአዲሱ ዓመት አዲስ ትልም በመንደፍ ስኬት የምናሳካበት ዘመን ይሆናል ብሎ ማህበራችን ያምናል። አዲስ ዓመት አዲስ ታሪክ ለመጻፍ የተሰጠን ንጹሕ ገጽ በመሆኑ ለትውልድ የሚሻገር መልካም ስራ መስራት ተገቢ ነው። ትናንትን መለወጥ ባንችልም እንኳን፤ ነገን ግን በአዲስ ማንነትና በጠንካራ ሥራ ማሸብረቅ ዘመን ተሻጋሪ ማድረግ እንችላለን። ዘመን መለወጡ ሳይሆን ቁም ነገሩ በተለወጠው ዘመን ላይ ሁነን በአንድነት የምንሰራው ሥራ ነው ወሳኙ ነገር። አዲሱ ዓመት በህልውና ትግል ውስጥ ላለው ህዝባችን ፍትህ የሚጎናጸፍበት እንዲሆን ማህበራችን ጠንካራ ምኞቱ ነው። ለዚህም ከጠንካራ አባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር በመሆን የሰብአዊ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል። በዚህ አጋጣሚ ማህበረሰባችን በክልሉ ላሉ የድርቅ፣ የመፈናቀልና የጦርነት አደጋዎች ለተጋለጡ ወገኖች ድጋፉን እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። መልካም አዲስ አመት! “የቀደመውን ነገር አታስቡ፤ ያለፈውን እርሱ።እነሆ፤ አዲስ ነገር አደርጋለሁ! እርሱም አሁን ይበቅላል፤ አታስተውሉትምን? በምድረ በዳም መንገድ አዘጋጃለሁ፤ በበረሓም ምንጭ አፈልቃለሁ።” ኢሳ 43፡18
