እንኳን ለደመራ በዓል አደረሳችሁ የአማራ ማህበር በኦሪገን እንኳን ለ2019 ዓ.ም የደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልጻል። በዓሉን ስናከብር በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችንን በማሰብ እንዲሆን ያሳስባል።
Meeting Reminder Amhara Association of Oregon would like to invite all Amhara community and supporters to attend a virtual meeting on October 3rd 2026 at 8 pm. Miss it not!
ተመድ በኢትዮጵያ በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰው ግድያ አሳስቦኛል አለ በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ሁኔታና የድሮን ጥቃት አሳስቦኛል ሲል የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ አስታወቀ በኢትዮጵያ ፈጽሞ በተለየ ሁኔታ እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ሁኔታና በቅርብ ጊዜ በኢትዮጵያ የተከሰቱት ክስተቶች፣ አዲስ የታጠቁ ቡድኖች ጥምረት መመስረትና ቀጣይነት ያለው የጸጥታ ችግር እንዲሁ በዘፈቀደ የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶችና በንጹሃን ዜጎች ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን አስመልክቶ የሚደርሱ ሪፖርቶች በጣም አሳሳቢ መሆናቸውን በቃለ አቀባዩ በኩል ተገልጿል። በከፍተኛ ውጥረት ወቅት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሁኔታውን የበለጠ ሊያባብሱ ከሚችሉ ድርጊቶች ወይም ንግግሮች እንዲቆጠቡ፤ ችግሮችን በውይይት እንዲፈቱ እናሳስባለን ያለው ሪፖርቱ ወታደራዊ እርምጃ የፖለቲካ ልዩነቶችን ወይም መሰረታዊ ቅሬታዎችን አይፈታም ብሏል። በአማራ፣ በትግራይና በኦሮምያ በመንግስት ወታደሮች በርካታ ንጹሃን ዜጎች በግፍ እየተገደሉ፣ እየተፈናቀሉ ለስደት እየተዳረጉ መሆኑን ላለፉት ሰባት ዓመታት በመገናኛ ብዙሃን ሲዘገብ መቆየቱና የተባበሩት መንግስታት በጉዳዩ ዙሪያ ምንም ትኩረት አለመስጠቱ የሚታወስ ነው።
ድርቅ በአማራ ክልል በአማራ ክልል ያለው የሰብአዊ ቀውስ እየተባባሰ መሆኑ ኗሪዎቹ እየገለጹ ነው። በተለያዩ ብዙሃን መገናኛ አውታሮች በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ አማካይነት ከስፍራው የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአገዛዙ ከሚፈጸም የጅምላ የድሮንና የከባድ መሣሪያ ጭፍጨፋ በተጨማሪ በተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች በከፍተኛ ድርቅ እየተመቱ ነው። እንስሳት የሚበሉት መኖ አጥተው እየሞቱ ነው፤ የተዘሩ ሰብሎችም ለፍሬ ሳይበቁ እየደረቁ ነው፤ ዝናብን ተስፋ አደርገው የታረሱ ማሳዎች ጦም አድረዋል። በርካታ ሰዎችም ቤታቸውን በመዝጋት ህይዎታቸውን ለማትረፍ ወደ ከተማ እየተሰደዱ ሲሆን የአገዛዙ አመራሮች “ገጽታን ያበላሻሉ” በማለት ወደ ዋና ዋና ከተሞች እንዳይገቡ በማድረግ በቀያቸው ሆነው ያለምንም እርዳታ እንዲሞቱ እየተፈረደባቸው መሆኑን ተዘግቧል። ድርቁ በአማራ ክልል በጎንደር ጠለምትና በዋግ ኽምራ ወረዳዎች ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን በአካባቢው ያሉ ኗሪዎች የተናገሩ ሲሆን በሀገሪቱ የተከሰተው ድርቅ አድማሱን በማስፋት በትግራይና በአፋርም እንስሳት እየሞቱና ኗሪውም ቀየውን ለቅቆ እየተሰደደ መሆኑ ተዘግቧል። አፋጣኝ ድጋፍ ማድረግ ካልተቻለ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ ቀውስ ሊከሰት እንደሚችል ተገልጿል። የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት መንግስት ለሚያጎርሰው ሳይሆን በጅምላ ለሚተኩሰው የጦር መሣሪያ ትኩረት ማድረጉ አሳዛኝ ነው ሲሉ በርካታ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ያስረዳሉ።
እንቁጣጣሽ! መልካም አዲስ አመት እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት አደረሳችሁ! የአማራ ማህበር በኦሪገን ለማህበሩ አባላትና ለመላው ኢትየጵያውያን አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ ይላል። ከአሮጌው ዘመን በመማር ለአዲሱ ዓመት አዲስ ትልም በመንደፍ ስኬት የምናሳካበት ዘመን ይሆናል ብሎ ማህበራችን ያምናል። አዲስ ዓመት አዲስ ታሪክ ለመጻፍ የተሰጠን ንጹሕ ገጽ በመሆኑ ለትውልድ የሚሻገር መልካም ስራ መስራት ተገቢ ነው። ትናንትን መለወጥ ባንችልም እንኳን፤ ነገን ግን በአዲስ ማንነትና በጠንካራ ሥራ ማሸብረቅ ዘመን ተሻጋሪ ማድረግ እንችላለን። ዘመን መለወጡ ሳይሆን ቁም ነገሩ በተለወጠው ዘመን ላይ ሁነን በአንድነት የምንሰራው ሥራ ነው ወሳኙ ነገር። አዲሱ ዓመት በህልውና ትግል ውስጥ ላለው ህዝባችን ፍትህ የሚጎናጸፍበት እንዲሆን ማህበራችን ጠንካራ ምኞቱ ነው። ለዚህም ከጠንካራ አባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር በመሆን የሰብአዊ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል። በዚህ አጋጣሚ ማህበረሰባችን በክልሉ ላሉ የድርቅ፣ የመፈናቀልና የጦርነት አደጋዎች ለተጋለጡ ወገኖች ድጋፉን እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። መልካም አዲስ አመት! “የቀደመውን ነገር አታስቡ፤ ያለፈውን እርሱ።እነሆ፤ አዲስ ነገር አደርጋለሁ! እርሱም አሁን ይበቅላል፤ አታስተውሉትምን? በምድረ በዳም መንገድ አዘጋጃለሁ፤ በበረሓም ምንጭ አፈልቃለሁ።” ኢሳ 43፡18
ዘመን በባተ ቁጥር ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ይነገራል። ለግንዛቤ ቀጣዩን ጽሑፍ አንብቡት። የኢትዮጵያ ዘመን አቈጣጠር በዲያቆን ኃይለ ኢየሱስ ቢያ መስከረም ፮ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም የዘመን አቈጣጠር ዓመታትን፣ ወራትን፣ ሳምንታትን፣ ዕለታትን፣ ደቂቃን እና ድቁቅ ሰዓታትን በየሥፍራቸው (በየመጠናቸው) የሚገልጽ፤ የሚተነትን፤ የሚለካ የቤተ ክርስቲያን የቍጥር ትምህርት ነው፡፡ እነዚህ ዅሉ ተመርምረው፣ ተመዝነው፣ ተቈጥረው ሲያበቁ ምድብና ቀመር ተሰጥቷቸው የሚገኙበትን ውሳኔና ድንጋጌ የሚያሳውቅ የዘመን አቈጣጠር – ‹ሐሳበ ዘመን› ይባላል፡፡ ዓመታት፣ ወራት፣ ሳምንታት፣ ዕለታትና ሰዓታት የሚለኩት (የሚሠፈሩት፣ የሚቈጠሩት) በሰባቱ መሥፈሪያና በሰባቱ አዕዋዳት ነው፡፡ ሰባቱ መሥፈርታት የሚባሉትም፡- ሳድሲት፣ ኃምሲት፣ ራብዒት፣ ሣልሲት፣ ካልዒት፣ ኬክሮስ እና ዕለት ሲኾኑ ሰባቱ አዕዋዳት ደግሞ፡- ዐውደ ዕለት፣ ዐውደ ወርኅ፣ ዐውደ ዓመት፣ ዐውደ ፀሐይ፣ ዐውደ አበቅቴ፣ ዐውደ ማኅተም እና ዐውደ ቀመር ናቸው፡፡ ዐውደ ዕለት – ከእሑድ እስከ ቅዳሜ ያሉት ሰባቱ ዕለታት ሲኾኑ፤ አውራኅን (ወራትን) ለማስገኘት በዚህ ሲመላለሱ ይኖራሉ፡፡ ዐውደ ወርኅ – በፀሐይ ፴ ዕለታት፣ በጨረቃ ፳፱ ወይም ፴ ዕለታት ናቸው፤ ዓመታትን ለማስገኘት በዚህ ሲመላለሱ ይኖራሉ፡፡ ዐውደ ዓመት – በፀሐይ ቀን አቈጣጠር ፫፻፷፭ ቀን ከ፲፭ ኬክሮስ፤ በጨረቃ አቈጣጠር ፫፻፶፬ ቀን ከ፳፪ ኬክሮስ ነው፡፡ እነዚህ ሦስቱ በዕለት፤ አራቱ ደግሞ...Read More