ለሰብአዊነት ቅድሚያ ይሰጣል

ፖርትላንድ፡ሚያዚያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ወደ አንድነት መምጣቱ ለሰብአዊነት የሚሰጠውን ትኩረት ከፍ አድርጎታል ሲሉ የድርጅቱ አመራሮች ገለጹ። ይህ የተገለጸው  የአማራ ማህበር በኦሪገን በአማራ ክልል ሰብአዊ ቀውስን ለመቀነስ ንቅናቄው ምን እየሰራ እንደሆነ ተጠይቆ ለተሰብሳቢዎቹ አመራሮች ማብራሪያ በሰጡበት ስብሰባ ላይ ነው። ንቅናቄው ዓለም ዓቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን አክብሮ የሚሰራ መሆኑም ተረጋግጧል። በቅድሚያ ማብራሪያ የሰጡት የአፋብን ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ አስረስ ማረ ሲሆኑ በማብራሪያቸውም ፋኖ የህብረተሰቡ ጥያቄ የነበረውን የአንድነት ጉዳይ በድል ካጠናቀቀ ጊዜ አንስቶ በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ አደጋዎች ሰዎች እንዳይጎዱ ቀጥታ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ችግሩን ለሚመለከታቸው አካላት በማድረስና እርዳታ እንዲደርሳቸው በማድረግ በኩል የተሻለ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ድርጅቱም በተመሰረተ በአጭር ጊዜ በርካታ ውሳኔዎችንና ትላልቅ ወታደራዊ ድሎች አስመዝግቧል። ይሁን እንጂ ድርጅቱ ዲያስፖራውን በማደራጀት እና ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግ በማድረግ በኩል ብዙ ይቀራል ብለዋል። አገዛዙ ውጊያ ተዋግቶ ያሸነፈበት፣ የተረጋጋ አስተዳደራዊ መዋቅር ዘርግቶ መስራት እንዳይችል ከመደረጉም በላይ ትጥቅና ሥንቅ ከጠላቶቻችን በሚል መርህ ወታደራዊ ትግሎችን በማከናዎን ሁሉንም በድል በማጠናቀቅ ከፍተኛ የሆነ ትጥቅና...Read More

MISS IT NOT!

🚨 የህልውና እና የክብር ጥሪ፡ ለኦሪገን አማራ ማህበር አባላትና ደጋፊዎች "ታሪክ የሚሰራው በሚሳተፉት እንጂ በታዛቢዎች አይደለም!" በቅድሚያ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የክርስቶስ ትንሳኤ ለህዝባችን የተስፋ፣ የድልና የነፃነት ብርሃን እንዲሆንልን ከልብ እንመኛለን። ነገር ግን በዓሉን ስናከብር፣ ወገናችን የሚገኝበትን እጅግ አስቸጋሪና ፈታኝ ወቅት መዘንጋት አይገባንም። አሁን ያለንበት ወቅት የቆረጡ ልጆች እንጂ የዳር ተመልካች የማይሻበት ጊዜ ነው። ማህበራችን ይህንን ታሪካዊ ግዴታ ለመወጣት የእያንዳንዱን አባልና ደጋፊ ንቁ ተሳትፎ የግድ ይላል። ለምን መገኘትዎ ግዴታ ነው? * ሶስት ልዩ ተጋባዥ እንግዶች፦ በወቅታዊው የህዝባችን ሁኔታና በቀጣይ ስራዎቻችን ላይ ጥልቅ ትንታኔና መመሪያ የሚሰጡን ሶስት አንጋፋ እንግዶች በሰዓቱ ተገኝተው ንግግር ያደርጋሉ። * የወደፊት አቅጣጫ፦ የስብሰባው ዋና አላማ የማህበራችንን የቀጣይ ጊዜያት ስትራቴጂያዊ እርምጃዎች ለመወሰንና የጋራ አቋም ለመያዝ ነው። * አንድነታችንን ማሳያ፦ በስብሰባው ላይ በብዛት መገኘታችን ለጠላቶቻችን መለኪያ፣ ለወዳጆቻችን ደግሞ ጥንካሬ ነው። 📅 ቀን፦ ዓርብ፣ ኤፕሪል 17፣ 2026 (Friday, April 17) 🕗 ሰዓት፦ በትክክል ምሽት 8:00 PM (Pacific Time) 🔗 የZoom መግቢያ ሊንክ፦ እዚህ ይጫኑና ይግቡ 📌 Meeting ID:...Read More

በዋግኽምራ ዞን በድርቅ ምክንያት ከ4 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተሰደዱ

በዋግኽምራ ዞን በድርቅ ምክንያት ከ4 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተሰደዱ አንዳንዶች ልጆቻቸውን ለልመና እያሰማሩ መሆኑ ተገልጧል ህጻናትን ለልመና የሚያሰማሩ አካላት ላይ መንግስት ጥብቅና ሕጋዊ ርምጃ ለመውሰድ የዞን ግብረ ኃይል ማደራጀቱን ዐሳውቋል በአማራ ክልል በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን፣ ፃግብጂ ወረዳ በሚገኙ አራት ቀበሌዎች በተከሰተ ድርቅ ምክንያት ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ቀዬያቸውን ጥለው ወደ ተለያዩ ከተሞች መሰደዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና መምህራን ገለጹ። በርካታ ህጻናት ትምህርታቸውን አቋርጠው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ደሴና ሌሎች ከተሞች በመሰደድ በልመና ተግባር ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙም ተገልጧል ። በደሴ ከተማ በልመና ላይ የሚገኙ የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች፦ ስደቱ የተከሰተው በአካባቢያቸው የሚበላ ነገር በመጥፋቱና በድርቁ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። መምህራን በበኩላቸው ስደቱ በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠሩን ገልጸው፣ አንዳንዶች ልመናን እንደ ገቢ ምንጭ በመጠቀም ልጆቻቸውን ለልመና እያሰማሩ መሆኑንም ተናግረዋል ። የዞኑ አደጋ መከላከልና ሥራ አመራር ኮሚሽን በበጋው ወቅት ሰብላቸው ለተጎዳባቸው 27 ሺህ ሰዎች የምግብና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል። የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩ እንደገለጹት፦ በትክክል በችግር ምክንያት የተሰደዱትን ነዋሪዎች ወደ ቀዬያቸው በመመለስ ድጋፍ የማድረግ ሥራ እየተሠራ መሆኑን...Read More

Meeting reminder

Date: [video width="1920" height="1080" mp4="http://oregonamhara.org/wp-content/uploads/2026/04/Edited-meeting-promo.mp4"][/video] April 17, 2026 Time: At 8 pm Venue: zoom meeting

የስብሰባ ጥሪ

የስብሰባ ጥሪ በኦሪገን የአማራ ማህበር “ተገናኝተን የምንመክርበት ጊዜው አሁን ነው፤ ስለ አማራ የምንመክርበት ጊዜው አሁን ነው፤ በጋራ በመቆም ልዩነት የምንፈጥርበት ጊዜው አሁን ነው” እያለ የስብሰባ ጥሪውን ያስተላልፋል። ዛሬ ተገናኝተን በአንድነት ስለኣማራ ህዝብ መነጋገርና መደገፍ ካልቻልን መቼም ሊሆን አይችልም። ስለዚህ ዛሬ ከትላንትናው በተሻለ በአንድነት በመሆን አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅብናል። ስለሀገራችን በተለይም ደግሞ በአማራ ክልል ስላለው ሁኔታ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ ነው። በመሆኑም ማህበራችን ከአገር ቤት ካሉ የፋኖ አመራሮችን በቀጥታ በመጋበዝ በክልሉ ስላለው የሰብአዊ አያያዝ፣ የተፈናቃዮች ሁኔታና መደረግ ስላለበት ሰብአዊ ድጋፍ ማብራሪያ እንዲሰጡ ማህበሩ አነጋግሮ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ታዲያ ምን ይጠበቃል። የሚጠበቀው በኦሪገንና ዋሽንግተን ቫንኮበር ኗሪ የሆናችሁ የአማራ ተወላጆችና ደጋፊዎች በስብሰባው ላይ መታደም ብቻ። ከዚህም በተጨማሪ ማህበሩ የማህበሩ የስራ እንቅስቃሴ ይቀርባል። በሚደረገው ገለጻ ላይ ተመስርቶ ቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣል። ኑ እኛም የዚህ ታላቅ ህዝብ ልጆች ነንና በጋራ ሁነን ታላቅ ታሪክ እንስራ! በሚያልፍ ህይወት ላይ ሁነን ህያው ሥራ እንስራ። በኦሪገን የአማራ ማህበር Date: April 17 2026 place: Zoom meeting Time: 8 pm