ለሰብአዊነት ቅድሚያ ይሰጣል

ፖርትላንድ፡ሚያዚያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ወደ አንድነት መምጣቱ ለሰብአዊነት የሚሰጠውን ትኩረት ከፍ አድርጎታል ሲሉ የድርጅቱ አመራሮች ገለጹ። ይህ የተገለጸው  የአማራ ማህበር በኦሪገን በአማራ ክልል ሰብአዊ ቀውስን ለመቀነስ ንቅናቄው ምን እየሰራ እንደሆነ ተጠይቆ ለተሰብሳቢዎቹ አመራሮች ማብራሪያ በሰጡበት ስብሰባ ላይ ነው። ንቅናቄው ዓለም ዓቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን አክብሮ የሚሰራ መሆኑም ተረጋግጧል። በቅድሚያ ማብራሪያ የሰጡት የአፋብን ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ አስረስ ማረ ሲሆኑ በማብራሪያቸውም ፋኖ የህብረተሰቡ ጥያቄ የነበረውን የአንድነት ጉዳይ በድል ካጠናቀቀ ጊዜ አንስቶ በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ አደጋዎች ሰዎች እንዳይጎዱ ቀጥታ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ችግሩን ለሚመለከታቸው አካላት በማድረስና እርዳታ እንዲደርሳቸው በማድረግ በኩል የተሻለ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ድርጅቱም በተመሰረተ በአጭር ጊዜ በርካታ ውሳኔዎችንና ትላልቅ ወታደራዊ ድሎች አስመዝግቧል። ይሁን እንጂ ድርጅቱ ዲያስፖራውን በማደራጀት እና ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግ በማድረግ በኩል ብዙ ይቀራል ብለዋል። አገዛዙ ውጊያ ተዋግቶ ያሸነፈበት፣ የተረጋጋ አስተዳደራዊ መዋቅር ዘርግቶ መስራት እንዳይችል ከመደረጉም በላይ ትጥቅና ሥንቅ ከጠላቶቻችን በሚል መርህ ወታደራዊ ትግሎችን በማከናዎን ሁሉንም በድል በማጠናቀቅ ከፍተኛ የሆነ ትጥቅና...Read More