የስብሰባ ጥሪ

የስብሰባ ጥሪ
በኦሪገን የአማራ ማህበር “ተገናኝተን የምንመክርበት ጊዜው አሁን ነው፤ ስለ አማራ የምንመክርበት ጊዜው አሁን ነው፤ በጋራ በመቆም ልዩነት የምንፈጥርበት ጊዜው አሁን ነው” እያለ የስብሰባ ጥሪውን ያስተላልፋል። ዛሬ ተገናኝተን በአንድነት ስለኣማራ ህዝብ መነጋገርና መደገፍ ካልቻልን መቼም ሊሆን አይችልም። ስለዚህ ዛሬ ከትላንትናው በተሻለ በአንድነት በመሆን አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅብናል። ስለሀገራችን በተለይም ደግሞ በአማራ ክልል ስላለው ሁኔታ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ ነው። በመሆኑም ማህበራችን ከአገር ቤት ካሉ የፋኖ አመራሮችን በቀጥታ በመጋበዝ በክልሉ ስላለው የሰብአዊ አያያዝ፣ የተፈናቃዮች ሁኔታና መደረግ ስላለበት ሰብአዊ ድጋፍ ማብራሪያ እንዲሰጡ ማህበሩ አነጋግሮ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ታዲያ ምን ይጠበቃል። የሚጠበቀው በኦሪገንና ዋሽንግተን ቫንኮበር ኗሪ የሆናችሁ የአማራ ተወላጆችና ደጋፊዎች በስብሰባው ላይ መታደም ብቻ። ከዚህም በተጨማሪ ማህበሩ የማህበሩ የስራ እንቅስቃሴ ይቀርባል። በሚደረገው ገለጻ ላይ ተመስርቶ ቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣል። ኑ እኛም የዚህ ታላቅ ህዝብ ልጆች ነንና በጋራ ሁነን ታላቅ ታሪክ እንስራ! በሚያልፍ ህይወት ላይ ሁነን ህያው ሥራ እንስራ።
በኦሪገን የአማራ ማህበር

Date: April 17 2026

place: Zoom meeting

Time: 8 pm

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *