Blog

Meeting reminder

Date: [video width="1920" height="1080" mp4="http://oregonamhara.org/wp-content/uploads/2026/04/Edited-meeting-promo.mp4"][/video] April 17, 2026 Time: At 8 pm Venue: zoom meeting

የስብሰባ ጥሪ

የስብሰባ ጥሪ በኦሪገን የአማራ ማህበር “ተገናኝተን የምንመክርበት ጊዜው አሁን ነው፤ ስለ አማራ የምንመክርበት ጊዜው አሁን ነው፤ በጋራ በመቆም ልዩነት የምንፈጥርበት ጊዜው አሁን ነው” እያለ የስብሰባ ጥሪውን ያስተላልፋል። ዛሬ ተገናኝተን በአንድነት ስለኣማራ ህዝብ መነጋገርና መደገፍ ካልቻልን መቼም ሊሆን አይችልም። ስለዚህ ዛሬ ከትላንትናው በተሻለ በአንድነት በመሆን አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅብናል። ስለሀገራችን በተለይም ደግሞ በአማራ ክልል ስላለው ሁኔታ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ ነው። በመሆኑም ማህበራችን ከአገር ቤት ካሉ የፋኖ አመራሮችን በቀጥታ በመጋበዝ በክልሉ ስላለው የሰብአዊ አያያዝ፣ የተፈናቃዮች ሁኔታና መደረግ ስላለበት ሰብአዊ ድጋፍ ማብራሪያ እንዲሰጡ ማህበሩ አነጋግሮ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ታዲያ ምን ይጠበቃል። የሚጠበቀው በኦሪገንና ዋሽንግተን ቫንኮበር ኗሪ የሆናችሁ የአማራ ተወላጆችና ደጋፊዎች በስብሰባው ላይ መታደም ብቻ። ከዚህም በተጨማሪ ማህበሩ የማህበሩ የስራ እንቅስቃሴ ይቀርባል። በሚደረገው ገለጻ ላይ ተመስርቶ ቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣል። ኑ እኛም የዚህ ታላቅ ህዝብ ልጆች ነንና በጋራ ሁነን ታላቅ ታሪክ እንስራ! በሚያልፍ ህይወት ላይ ሁነን ህያው ሥራ እንስራ። በኦሪገን የአማራ ማህበር Date: April 17 2026 place: Zoom meeting Time: 8 pm

ዓፄ ፋሲለደስ

ዓፄ ፋሲለደስ ወይም ዓፄ ፋሲል (የዙፋን ስማቸው ዓለም ሰገድ) ከአባታቸው ከአፄ ሱሰኒዮስ እና ከእናታቸው ልዕልት ስልጣነ ሞገስ፣ ህዳር 10፣ 1603 (እ.ኤ.አ) ተወለዱ። የነገሱበትም ዘመን ከ1632 እስከ ጥቅምት 18, 1667 (እ.ኤ.አ) ነበር። ንግስና በስረፀ ክርስቶስ በተመራው አመፅ ምክንያት በ1630 ፋሲለደስ ለንግስና ቢበቃም፣ ዘውዱን ግን እስከ 1632 አልጫነም ነበር። ሲመተ ንግስናው በ1632 እንደተገባደደ የመጀመሪያው ስራው የተዋህዶ ቤ/ክርስቲያንን የቀድሞው ቁመና መመለስና የካቶሊኮችን መሬት በመቀማት ከደንካዝ በማባረር በፍሪሞና እንዲወሰኑ ማድረግ ነበር። ወዲያውም በማከታተል ከግብፅ አገር አዲስ ጳጳስ እንዲላክለት በማድረግ በአባቱ ዘመን እንዲደበዝዝ ተደርጎ የነበረውን የግብፅና ኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ግንኙነት እንዲጸና አደረገ። በኬኒያ የሚገኘው የሞምባሳ ወደብ በፖርቱጋሎች መደብደቡን ሲሰማ፣ የሮማው ፓፓ ከበስትጀርባው ያለበት ሴራ ነው በማለት በምድሩ የነበሩትን የካቶሊክ ጀስዊቶች በመሰብሰብ አባረራቸው።   ጎንደር ከተማ ፋሲለደስ የጎንደር ከተማን በ1636 የኢትዮጵያም ዋና ከተማ አድርጎ እንደቆረቆራት ይታመናል።[1] ከሱ በፊት በአካባቢው ከተማ እንደነበር ወይም እንዳልነበር በታሪክ የተገኘ ማስርጃ እስካሁን የለም። አከታትሎም የፋሲል ግቢንና 44ቱ ታቦታት ተብለው የሚታወቁትን የጎንደር ከተማ አብያተ ክርስቲያናት መሰረት ጣለ። በአፄ ፋሲል ከተመሰረቱት ታዋቂወቹ 44 አብያተ ክርስቲያናት፣ ታዋቂወቹ አደባባይ እየሱስ፣ አደባባይ ተክለ ሃይማኖት፣ አጣጣሚ ሚካኤል፣ ግምጃቤት ማሪያም፣ ፊት ሚካኤል፣ እና ፊት አቦ ይገኙበታል።[2] ያለመታከትም 7 የድንጋይ ድልድዮችን በማሰራት እስካሁን ድረስ ስሙ ሲጠራ...Read More

ከሀገር ቤት የተላከ ደብዳቤ

ይድረስ ለልጆቼ ከአባታችሁ። እንዴው ለመሆኑ ሰላም አላችሁ? ጤንነታችሁ እንዴት ነው? እኛ ደህና ነን። እድሜ ለእናንተ ደህና ነን። እንዴው ሁኔታው ግን ያስፈራል። ግፉ በዛ። ሞት በሁሉም ቤት እየገባ ነው። የኛ ተራም እስኪደርስ ድረስ እንቆዝማለን። ለመሆኑ አማሪካ ችግር ገጠማት እንዴ? በሰልፍ ተናወጠች ብሎ እኮ የአያ ጥላሁን ልጅ በሰፊው አጫወተኝ። ይገርምሃል ትምህርቱን ከዩኒበርስቲ ተመርቆ ከተመለሰ ጊዜ ጀምሮ ስለ ውጭው እና ስለ ሀገራችን በሞባይሉ ይነግረኛል። እንዲያ እሳት የነበረ ተማሪ ኮሌጅ በጥሶ ከእኔ ከሽማግሌው ጋር ሰፈር ለሰፈር ሲውል እንዴት አንጀት ይበላል መሰለህ። የመንግስት ሹማምንት ይመጡና ውትድርና ልውሰድህ እያሉ ስለሚያስቸግሩት እነሱ መጡ በተባለ ቁጥር ጫካ ውስጥ እየዋለ እያደረ ያመልጣቸዋል። ከሰሞኑ መጥተው ቢያጡት ያን ጠንካራ ገበሬ አባቱን ካላመጣኽው እንደፋሃለን ብለውታል። አስጨናቂ ጊዜ ነው ልጆቼ። የራሳችን ጎረቤቶች ወረዳ ሂደው እየጠቆሙ ስንቱን ወጣት ወደ ውትድርና እንዲጋዝ አደረጉት መሰለህ። የእኔ ነገር ለመሆኑ ምን ይፈጠር ብላችሁ ነው በአማሪካ ላይ ሰልፍ የወጣችሁት። ሰው በሃገሩ ስንት ግፍ እየደረሰበት ተሸክሞ ዝም ብሎ የለም እንዴ! መቼም ያልታደለ አማራ ይውጣ አልተባለም አይደል? መቼም የእኛ ጉደኞች እንደሚያደርጉት...Read More

ኢድ ሙባረክ

ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች እንኳን 1447ኛው ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ኢድ ሙባረክ/ረመዳን ሙባረክ የአማራ ማህበር በኦሪገን

ማህበሩን ለማጠናከር ውይይት ተካሔደ

በኦሪገንና ዋሽንግተን ቫንኮበር የአማራ ማህበር ሥራ አመራሮች ማህበሩን ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ። (ኦሪገን፣ 3/15/2026) በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ሁሉን አቀፍ የሰብአዊ ቀውስ ላይ የአማራ ተወላጆች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ለማስቻል እየተሰራ ነው።  በኦሪገን ሀገረ ግዛት ውስጥ በርካታ የአማራ ተወላጆችና ደጋፊዎች ይኑሩ እንጂ በአንድነት ተሰባስበው  አስተዋጽኦ ከማድረግ አንጻር ብዙ እንደሚቀር ተወያይተዋል። ይህንን የዝምታ አካሄድ ለመስበርና ለማሰባሰብ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም አባላቱን ለማሰባሰብ በጥንካሬ ለመስራት ተወያይተዋል። በኦሪገንና ዋሽንግተን ቫንኮበር ግዛት ውስጥ የሚኖሩ አማራዎችንና ደጋፊዎችን በመለየት በአካል፣ በስልክና በሌሎች የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ማህበሩ እስካሁን ያደረጋቸውን የሰብአዊ ድጋፎችና የመሳሰሉ ስራዎችን በማስረዳት ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ ቢያደርግ ደግሞ የበለጠ ሥራ መሥራት እንደሚቻል ግንዛቤ በመፍጠር አባላቱን የማሰባሰብና የማስፋት ስራዎችን አጠናክረው ለመስራት አጽንኦት ሰጥተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ሀገር ቤት ያለውን የአማራ ክልል ነባራዊ ሁኔታና የሰብአዊ አያያዝ በተመለከተ በቦታው የሚገኙ የፋኖ አመራሮችን በመጋበዝ ለአባላቱ ማብራርያ እንዲሰጡ ለማድረግ እንዲሰራ ወስነዋል። የአማራ ህዝብ በዘርፈ ብዙ ችግሮች ውስጥ ያለ መሆኑን መረዳት አስፈላጊ መሆኑን የተነጋገሩ ሲሆን በኦሪገን የሚኖሩ ሁሉ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ...Read More

War updates from Amhara Region, Ethiopia – February 16th to 22nd, 2026

Overview   For the week of February 16th to 22nd, 2026, fighting between the Amhara Fano self-defense force (Fano) and Oromo Prosperity Party regime joint forces (regime forces) has continued in various parts of Amhara Region in Ethiopia.   This week battle events and rights violations were recorded in more than 36 woreda/city administrations across 10 zonal administrations in Amhara Region. These zones included Wag-Hemra, North Wollo, South Wollo, North Shewa, East Gojjam, West Gojjam, North Gojjam, South Gonder, Central Gonder and West Gonder Zones.   Civilian casualties were recorded in 15 woreda/city administrations across 7 zonal administrations in Amhara Region. These included Gubalafto, Mekdela, Wegdi, Efratana-Gidim, Minjar-Shenkora, Kewet, Antsokiyana-Gemza, Gozamin, Finote-Selam, Jabi-Tehnan, Wemberima, Quarit, North Mecha, Bahir-Dar-Zuriya and Alefa Woredas in North Wollo, South Wollo, North Shewa, East Gojjam, West Gojjam, North Gojjam and Central Gonder Zones.   Arrests were recorded in Kobo City and Raya-Alamata Woredas of North...Read More

የአድዋ ድል ታሪክ

የአድዋ ጦርነት በየካቲት ፳፫ ቀን ፲፰፻፹፰ ዓ.ም. በኢትዮጵያና ኢጣሊያ መካከል የተካሄደ ውጊያ ሲሆን የአንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነት ክፍል ነው። በኢትዮጵያ አሸናፊነት የጣልያን የቀኝ ግዛት ማስፋፋት ተኮላሸ። ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ ' ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ፤ ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ መድፍ አገላባጭ ብቻለብቻ፤ የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው፤ የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኅተም፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል ነው፡፡ የመላው ዓለም ተፈጥሮአዊ ግብር እና ሰብአዊ ክብር የታደሠው፤ በእውነትና በፍትህ ህልውናና ምልዓት ላይ የተሰካ ትልቅ ጥርስ የተነቀለው … በአድዋ የታላቅ ህዝቦች ታላቅ ድል ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ስንሄድ 1066 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ታላቁ ጦርነት የተደረገበትና ታላቁ ድል የተገኘበት ሥፍራ አድዋ ከተማና የከተማው ግድም ገመገሞች ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያውያን አቡሻኽር (Julian calendar) የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም፤ ወይም በአውሮጳውያን የዘመን አቆጣጠር (Gregorian Calendar) February (የካቲት) መጨረሻ እና March (መጋቢት) መጀመሪያ ላይ 1896. ለጦርነቱ መነሻ የሆነው ውል የተፈፀመው በዚሁ ዘመን ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 468 ኪሎ ሜትር ርቀት ግድም ከውጫሌ ከተማ ግርጌ ከአምባሰል ተራራ ሥር...Read More

እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

  የአድዋ ጦርነት የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ኢትዮጵያውያን በዐፄ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ ብሩር መሪነት ጣሊያንን በአድዋ ያሸነፉበት ታሪካዊ ድል ነው። ጦርነቱ የመጣው ጣሊያን በውል ንግግር (ውጫሌ ውል አንቀጽ 17) ሰበብ ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ለመያዝ ሙከራ በማድረጓ ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያን በፅናት በመዋጋት የቅኝ አገዛዝ ሙከራውን አክሽፈውታል። የአድዋ ጦርነት ዋና ዋና ነጥቦች፦ የጦርነቱ መንስኤ፦የውጫሌ ውል አለመግባባት፣ ጣሊያን አጠቃላይ ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ያደረገችው ህገ-ወጥ ጥረት። መሪዎች፦ዐፄ ምኒልክ፣ እቴጌ ጣይቱ፣ ራስ መኮንን፣ ራስ አሉላ፣ ራስ ਮੰገሻ እና ሌሎችም በጋራ ተዋግተዋል። የድል ቀን፦የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም (March 1, 1896)። ውጤት፦ጣሊያን በከፍተኛ ሁኔታ ተሸንፋ የ«ውጫሌ ውል»ን በመሰረዝ የኢትዮጵያን ነፃነት አምናለች። ታሪካዊ ፋይዳ፦ጥቁር ህዝቦች በነጮች ቅኝ ገዢዎች ላይ የተቀዳጁት የመጀመሪያው ትልቅ ድል በመሆኑ፣ ለታላቁ የአፍሪካ አንድነት እና ለቀለም አቀፍ ትግል ትልቅ ስንቅ ሆኗል።

ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ (አባ ታጠቅ) ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ

ጀግናዉ ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ (ጥር ፮ ቀን ፲፰፻፲፩ ዓ.ም. እስከ  ሚያዝያ ፮ ቀን፲፰፻፷ ዓ.ም.) ከ፲፰፻፵፯ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታችው ድረስ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። በትውልድ ስማቸው ካሳ ኀይሉ ሲባሉ፣ በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ፣ በወታደራዊ ስማቸው መይሳው ካሳና እንዲሁም አንድ ለናቱ ተብለው የሚታወቁ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ወታደርና ፖለቲከኛ ነበሩ። ቴዎድሮስ ጥር ፮ ቀን ፲፰፻፲፩ ዓ.ም. ሻርጌ በተባለ ቦታ ቋራ  ውስጥ፣ ከጎንደር ከተማ በስተ ምዕራብ ተወለዱ። የተወለዱትም አገሪቷ በባላባቶች ተከፋፍላ በምትመራበት-ዘመነ መሳፍንት በሚባለው ወቅት ነበር። አባታቸው ደጃዝማች ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ የቋራ ገዢ ነበሩ። ዓፄ ቴዎድሮስ በህጻንነታቸው የቄስ ትምህርት ከቀሰሙ በኋላ፣ የአጎታቸውንና በኋላም ለጥቂት ጊዜ የጎጃሙን ጦር መሪ የጎሹ ዘውዴን ጦር ተቀላቀሉ። በዚሁ የውትድርና ዘመናቸው ከፍተኛ ችሎታን ማስመዝገብ ስለጀመሩና ዝናቸው ስለተስፋፋ በ፲፰፻፴፱ ዓ.ም. በወይዘሮ መነን ሊበን አምዴ አነሳሽነት የልጇን የራስ አሊ አሉላን ልጅ፣ ተዋበች አሊን አገቡ፤ እንዲሁም በደጃዝማችነት ማዕረግ የቋራ አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ። ቴዎድሮስ ግን በ፲፰፻፵፬ ዓ.ም. አጠቃላይ የዘመነ መሳፍንት ሥርዓትን በመቃወም በሰሜናዊ ባላባቶች ላይ ዘመቻ ጀመሩ። በተከታታይ ዘመቻወች የገጠሟቸውን ባላባቶች ስላሸነፉ፣ መጀመሪያ የራስ ማዕረግን በኋላም የንጉሥ ማዕረግን በአንድ ዓመት ውስጥ ተቀዳጁ። በየጊዜው በሚያደርጉት የተሳካ ዘመቻ የዘመኑን ባላባቶች ኃይል በመሰባበር የካቲት ፫ ቀን ፲፰፻፵፯ ዓ.ም ንጉሥ ካሳ - ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ተብለው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆኑ። ሥርዓተ ንግሡ...Read More