Blog

ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ (አባ ታጠቅ) ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ

ጀግናዉ ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ (ጥር ፮ ቀን ፲፰፻፲፩ ዓ.ም. እስከ  ሚያዝያ ፮ ቀን፲፰፻፷ ዓ.ም.) ከ፲፰፻፵፯ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታችው ድረስ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። በትውልድ ስማቸው ካሳ ኀይሉ ሲባሉ፣ በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ፣ በወታደራዊ ስማቸው መይሳው ካሳና እንዲሁም አንድ ለናቱ ተብለው የሚታወቁ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ወታደርና ፖለቲከኛ ነበሩ። ቴዎድሮስ ጥር ፮ ቀን ፲፰፻፲፩ ዓ.ም. ሻርጌ በተባለ ቦታ ቋራ  ውስጥ፣ ከጎንደር ከተማ በስተ ምዕራብ ተወለዱ። የተወለዱትም አገሪቷ በባላባቶች ተከፋፍላ በምትመራበት-ዘመነ መሳፍንት በሚባለው ወቅት ነበር። አባታቸው ደጃዝማች ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ የቋራ ገዢ ነበሩ። ዓፄ ቴዎድሮስ በህጻንነታቸው የቄስ ትምህርት ከቀሰሙ በኋላ፣ የአጎታቸውንና በኋላም ለጥቂት ጊዜ የጎጃሙን ጦር መሪ የጎሹ ዘውዴን ጦር ተቀላቀሉ። በዚሁ የውትድርና ዘመናቸው ከፍተኛ ችሎታን ማስመዝገብ ስለጀመሩና ዝናቸው ስለተስፋፋ በ፲፰፻፴፱ ዓ.ም. በወይዘሮ መነን ሊበን አምዴ አነሳሽነት የልጇን የራስ አሊ አሉላን ልጅ፣ ተዋበች አሊን አገቡ፤ እንዲሁም በደጃዝማችነት ማዕረግ የቋራ አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ። ቴዎድሮስ ግን በ፲፰፻፵፬ ዓ.ም. አጠቃላይ የዘመነ መሳፍንት ሥርዓትን በመቃወም በሰሜናዊ ባላባቶች ላይ ዘመቻ ጀመሩ። በተከታታይ ዘመቻወች የገጠሟቸውን ባላባቶች ስላሸነፉ፣ መጀመሪያ የራስ ማዕረግን በኋላም የንጉሥ ማዕረግን በአንድ ዓመት ውስጥ ተቀዳጁ። በየጊዜው በሚያደርጉት የተሳካ ዘመቻ የዘመኑን ባላባቶች ኃይል በመሰባበር የካቲት ፫ ቀን ፲፰፻፵፯ ዓ.ም ንጉሥ ካሳ - ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ተብለው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆኑ። ሥርዓተ ንግሡ...Read More

በአማራ ክልል ከየካቲት 9 እስከ 15፣ 2026 ዓ.ም ጊዜ ውስጥ የተፈጸሙ ሰብአዊ ጥቃቶች

እ.ኤ.አ. ከየካቲት 9 እስከ 15 ቀን 2026 ዓ.ም ባለው የአንድ ሳምንት ጊዜ በአማራ ፋኖ ራስን መከላከል ሃይል (ፋኖ) እና በኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ አገዛዝ የጋራ ሃይሎች መካከል በኢትዮጵያ የተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ውጊያዎች ቀጥለዋል። በዚህ ሳምንት በአማራ ክልል በሚገኙ 11 የዞን አስተዳደሮች ከ37 በላይ ወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች  የጦር ድርጊቶችና የመብት ጥሰቶች የተፈፀሙ መሆኑ ታውቋል። ዋግ ኽምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ፣ መካከለኛውና ምዕራብ ጎንደር የሚገኙበት ሲሆን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞንና በአዲስ አበባ ከተማ የተመዘገቡ ለውጦችም እንደነበሩ የአማራ ማህበር በአሜሪካ የጥናት ቡድን አረጋግጧል። በራያ ቆቦ፣ በዋድላ፣ በኤፍራታና-ግድም፣ በቀወት፣ በምንጃር - ሸንኮራ፣ በቡሬ-ዙሪያ፣ በደብረታቦር ከተማና በፎገራ ወረዳዎች ጠንከር ያሉ ውጊያዎችና የሰብአዊና ጉዳትና የንብረት ውድመት አጋጥሟል። 39ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ በሚካሄድበት ጊዜ የከተማዋ ኗሪ የሆኑ በርካታ የአማራ ወጣቶችና ተቃዋሚ የፖለቲካ ሰዎች ላይ ኢላማ ኢላማ ተደርጎ በርካቶች ታፍሰው ወደ እስር ቤት ተግዘዋል፤ አንዳንዶች ደግሞ የት እንደ ደረሱ ማወቅ እንዳልተቻለ ለማዎቅ ተችሏል። ከ12 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ከሰፈራቸውና ከስራ ገበታቸው...Read More

የአማራን አንድነት ማጠናከር አንገብጋቢ ጉዳይ ነው

አንድነታችን ማጠናከር ወቅቱ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው ሲሉ በኦሪገን የአማራ ተወላጆች ገለጹ። በኦሪገን የአማራ ማህበር አጠቃላይ ስብሰባ ላይ አባላቱ እንደገለጹት በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብአዊ ቀውስ በሚቻለው መጠን ለመደገፍም ሆነ ለዓለም ድምጽ ለማሰማት በጋራ መቆም ወሳኝ መሆኑ በአጽንኦት አባላቱ ገልጸዋል። በ2025 ዓ.ም ማህበሩ በርካታ ስራዎችን መስራቱን በቀረበው ሪፖርት ለማወቅ ተችሏል። ከተሰሩ ስራዎች መካከልም በአገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ ለኦሪገን መንግስትና ለፌዴራል መንግስቱ የህዝብ እንደራሴዎች ተገቢው መረጃ እንዲደርሳቸው ተደርጓል። ከዚህም በተጨማሪ ለተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ የሚውል የገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ ተሰርቷል። የአባላት ቁርጠኝነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የማህበሩ አመራር የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ለማሰባሰብ ተሞክሯል። ይሁን እንጂ ጊዜን ሰጥቶ በቁርጠኝነት የመሰባሰብና የሚጠበቀውን ያህል አስተዋጽኦ ማድረግ አልተቻለም። አባላቱ በበኩላቸው የመረጃ ክፍተቶች እንደነበሩ ጠቁመው ይህን ክፍተት በማረም አጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን ትኩረት ተሰጥቶታል። በመንግስት እየተመራ በአማራ ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እየተከታተሉ ለአባላቱ፣ ለተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና ድርጅቶች፣ ለአሜሪካ ባለስልጣናት በማሳወቅ፣ የምናገኘውን ሚዲያ በመጠቀም ድምጻችንን በማሰማት ግፉ ፍጻሜ እንዲደርስና የአማራ ህዘብ ህልውና እንዲረጋገጥ በትጋት እንደሚሰራ አጽንኦት ተሰጥቶታል። የአማራ...Read More

A reminder, Saturday 14th of February 2026

Amhara Association Of Oregon is inviting you to a scheduled Zoom meeting. Topic: General  conference Time: Feb 14, 2026 08:00 PM Pacific Time (US and Canada) Join Zoom Meeting https://us06web.zoom.us/j/81548770702?pwd=xN3RTgrrXufVYRvS9uikvnOl1bZW5X.1 Meeting ID: 815 4877 0702 Passcode: 134457 --- One tap mobile +13462487799,,81548770702#,,,,*134457# US (Houston) +16694449171,,81548770702#,,,,*134457# US Join instructions https://us06web.zoom.us/meetings/81548770702/invitations?signature=EFkS87OTVN2MHEZUlT2y88QcMnlco0hhfKL_VVwK7Hc

እንኳን ለዐቢይ ጾምና ለሮመዳን ጾም አደረሳችሁ

በዚህ ሳምንት የሁለት አበይት አብያተ ዕምነቶች ሁለት ታላላቅ ጾሞች ተከታትለው ይጀመራሉ። ሰኞ የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን የሚጀምሩት ሊቀ ካህን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾሞ አማንያን ይጾሙት ዘንድ የተሰጠው ዐቢይ ጾም ወይም የሆዳዴ ጾም ይጀምራል። ከሁለት ቀን በኋላ ረቡዕ የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ደግሞ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚጾሙት የታላቁ የሮመዳን ጾም ይጀመራል። በኦሪገን የአማራ ማህበር እንኳን ለጾሙ በሰላም አደረሳችሁ ይላል። ነቢዩ ኢሳይያስ (58፤6-7) በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ስለጾም እንዲህ ይላል። “እኔስ የመረጥኩት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፣ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፤ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፣ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን? እንጀራህንስ ለተራበ ትቆርስ ዘንድ፣ ስደተኞችንና ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፣ የተራቆቱትንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፣ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሸግ አይደለምን?” ወንጌለኛው ቅዱስ ማቲዎስም (25፤35) ጾማችን ከጠብና ከሙግት በመራቅ ብቻ ሳይሆን መልካም ነገር በመስራት መሆን እንዳለበት የዓለም ቤዛ ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ያሰተማረውን እንዲህ ያዘክራል። “ተርቤ፣ አብልታችሁኛልና፣ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛል፣ እንግዳ ሁኜ ተቀብላችሁኛልና፣ ታርዤ አልብሳችሁልኛልና፣ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፣ ታስሬ ወደ እኔ...Read More

ሰምተዋል?

ሰምተዋል? በኦሪገን የአማራ ማህበር አጠቃላይ ስብሰባ በመጪው ቅዳሜ በኦን ላይን መጥራቱን? ከቤትዎ ሁነው በእጅ ሞባይልዎ ወይም በሚመችዎ የመገናኛ መሣሪያ በመጠቀም ስብሰባውን ይታደሙ። አደራ እንዳይቀሩ። ማህበርዎን ያጠናክሩ! አንድነት ኃይል ነው!

የአገዛዙ የግፍ ግድያ ባህር ዳር ከተማ!

በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ እየፈፀመ ያለው አገዛዝ ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸውን የሕክምና ዶክተሮችን፣ የነቁ አማራዎችንና ባለሐብቶችን በየቀኑ ከቤታቸው እየተጎተተ እያወጣ ማረዱን ቀጥሏል:: በመሆኑም ትላንት በቀን 26/05/2018ዓ.ም ዶ/ር ፀጋሁን ስሜ የሚባልን በምሥራቅ ጎጃም፣ የደብረወርቅ ተወላጅና የባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ነዋሪ እንዲሁም የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሠራተኛ የነበረውን ጥዋት ሥራ ለመግባት በጉዞ ላይ እያለ በአገዛዙ ወታደሮች ይያዛል። የአገዛዙ ወታደሮች ከያዙት በሗላ ወደ ቤቱ መልሰው በመውሰድ በቤቱ ፍተሻ ያደርጋሉ። ቤቱን በመፈተሽ ምንም ነገር ያላገኙት ወታደሮች ዶ/ር ፀጋሁንን ወደ ቤዛዊት ቤተመንግሥት አካባቢ ወስደው ገድለው ጥለውታል። የአገዛዙ ወታደሮች ዶ/ር ፀጋሁንን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉ በሗላ በማን አለብኝነት በራሱ ስልክ ለባለቤቱ በመደወል አስከሬኑን እንድትወስድ ይነግሯታል:: ዶ/ር ፀጋሁንን ምን እንዳነጋገሩት ባይታወቅም ከሳምንት በፊት የአማራ ክልል ጤና ቢሮው ኃላፊ የሆነው አብዱልከሪም መንግሥቱ ለብቻው ቢሮ እንዳነጋገረውና ከቢሮ ሲወጣም ጥሩ ስሜት እንዳልነበረው ጓደኞቹ ይናገራሉ:: ቤቱ ሲፈተሽም ምንም አይነት መረጃ እንዳልተገኘና የአገዛዙ ወታደሮችም የወሰዱት ማስረጃ እንደሌለ የዶ/ር ፀጋሁን ቤተሰቦች አረጋግጠዋል። በክልሉ ዋና ከተማ በባህር ዳር እንዲህ አይነት አሰቃቂ ግድያዎች...Read More

እንኳን ለከተራና ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በኦሪገንና በመላው ዓለም ለምትኖሩ የክረስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ2018 ዓ.ም ለኢየሱስ ክርስቶስ የከተራና የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት በኦሪገን የአማራ ማህበር መልካም ምኞቱን ይገልጻል። እስራኤላውያን ዮርዳኖስን በከተራው እንደተሻገሩት ሁሉ ሀገራችንም ወደ ተሟላ ሰላም የምትሻገርበት ጊዜ ይሁንልን። በጥምቀቱም ሰላምን፣ ፍቅርን አንድነትንና ለሰው ልጅ ትህትና የምናሳይበት እንዲሆን የአማራ ማህበር በኦሪገን ምኞቱን ይገልጻል። በዓሉን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖቻችንን እያሰብን እንዲሆን ማህበሩ ማሳሰብ ይወዳል። መልካም በዓል!

የአማራ ዜጎች ግድያ፣ መፈናቀል፣ እስራትና እገታ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ከታህሳስ 29፣ 2025 እስከ ጥር 4፣ 2026 ባለው የሳምንት ጊዜ ውስጥ በአማራ ፋኖ ራስን የመከላከል ኃይል (ፋኖ) እና በኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ አገዛዝ መካከል በተደረጉ ውጊያዎች ከ34 በላይ በሆኑ የአማራ ክልል ወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የአማራ ማህበር በአሜሪካ (AAA) በአወጣው ሳምንታዊ ጥናት አስታውቋል። ኢሰብአዊ ድርጊቱ የተፈጸመው በክልሉ ከሚገኙት የአስተዳደር መዋቅሮች ከኦሮሞ ልዩ ዞን ውጪ በሁሉም አካባቢዎች ነው። በተለይም ደግሞ በራያ ባላ፣ በቡግና፣ በስናን፣ በአዋበል፣ በአየሁ ጓጉሳ እና በምዕራብ ደምቢያ ወረዳዎች ሰላማዊ ሰዎች መጎዳታቸውን ጥናቱ አመላክቷል። በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ በአማራ ማህበረሰብ ላይ ጉዳት መድረሱም ተገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ወከባ፣ እስራትና የመፈናቀል ሥራዎች መቀጠላቸውን ጥናቱ ያሳያል። በአማራ ክልል በሚገኙ 3 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ የድሮን እንቅስቃሴ ተመዝግቧል። እነዚህም በምስራቅ ጎጃም ፣በምዕራብ ጎጃም እና በሰሜን ጎጃም ዞኖች ውስጥ የሚገኙትን የስናን፣ ጃቢ-ጠህናን እና የጎንጂ ቆለላ ወረዳዎችን ያጠቃልላል። በሁለቱ ክስተቶች የዜጎች ጉዳት ደርሷል። በአማራ ክልል በኮረም፣ በራያ ቆቦ፣ በአምባሰል፣ በሀብሩ እና በወምበርማ ወረዳዎች የሰላማዊ ሰዎች...Read More