Blog

Call for a Community Meeting

Call for a Community Meeting The Amhara Association of Oregon cordially invites all members and supporters to a community forum to discuss current issues affecting the Amhara community and explore ways to strengthen our unity, solidarity, and collective efforts. Date: October 3, 2026 Time: 8:00 PM Venue: Zoom Meeting ID: 874 2110 7512 Passcode: 594097 Our Unity, Our Strength, Our Future The Amhara people are facing critical challenges, including escalating violence, displacement, hunger, and poverty. Many of our people urgently need our solidarity, compassion, and support. As the Amhara saying goes, "The darkest hour is just before dawn." Despite the challenges we face, our unity, resilience, and collective action are essential to securing a better future for our people. Coming together and standing together is more important now than ever. Through unity, cooperation, and community service, we can strengthen our association and make a meaningful difference in the lives of...Read More

የስብሰባ ጥሪ

የስብሰባ ጥሪ የአማራ ማህበር በኦሪገን አባላቱና ደጋፊዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል። እንድትገኙ በአክብሮት ይጋብዛል። መቼ፡ October 3, 2026 @8 pm. ቦታ፡ በዙም/zoom መግቢያ ቃል፡ meeting ID 874 2110 7512, Pass code: 594097 ለአማራ ህልውና በጋራ ትግልና በማህበረሰብ አገልግሎት! ህዝባችንም ከፍ ሲል ማህበረሰባችን የወደፊት ዕጣ ፈንታችን ነው። የአማራ የህልውና ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ነው። በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈጸመው ግፍ እየተባባሰና በየቀኑ በርካቶችን እያፈናቀል በመኖርና ባለመኖር ውስጥ ገብተው የወገንን ድጋፍ ይማጸናሉ። ድጋፋችን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አሁን ያስፈልጋቸዋል። ''ሊነጋ ሲል ይጨልማል'' እንዲሉ አበውና እማው የነጻነታቸው ቀን እየተቃረበ ባለበት በአሁኑ ወቅት ዜጎቻችንን በርሃብና በርዛት ማጣት የሚያስቆጭ ነው የሚሆነው። በመሆኑም አንድነታችንንና ጥንካሬያችንን በተግባር በማሳየት መደገፍ ይገባናል። ለዚህ እውንነት ደግሞ መሰባሰብና በጋራ መቆም ወሳኝ ነው። እርስዎ  የአማራ ማህበር በኦሪገን አባል ነዎት? አባልነትዎ ማህበራችንንና ተልእኳችንን ያጠናክራልና እናመሰግናለን። ወርሃዊ የአባልነት ክፍያዎን እየከፈሉ ነው? ቀጣይነት ያለው ድጋፍዎ ማህበሩ የበለጠ እንዲሰራ ይረዳልና አጠናክረው እንዲቀጥሉ ማህበሩ ይጠይቃል። ለአባልነትና ድጋፍ ለማድረግ አስተባባሪዎችን ለማግኘት በዚህ ይደውሉ 9714298801 አንድነትና ትብብር...Read More

እንኳን ለደመራ በዓል አደረሳችሁ

የአማራ ማህበር በኦሪገን እንኳን ለ2019 ዓ.ም የደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልጻል። በዓሉን ስናከብር በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችንን በማሰብ እንዲሆን ያሳስባል።

Meeting Reminder

Amhara Association of Oregon would like to invite all Amhara community and supporters to attend a virtual meeting on October 3rd 2026 at 8 pm. Miss it not!

ተመድ በኢትዮጵያ በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰው ግድያ አሳስቦኛል አለ

በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ሁኔታና የድሮን ጥቃት አሳስቦኛል ሲል የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ አስታወቀ በኢትዮጵያ ፈጽሞ በተለየ ሁኔታ እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ሁኔታና በቅርብ ጊዜ በኢትዮጵያ የተከሰቱት ክስተቶች፣ አዲስ የታጠቁ ቡድኖች ጥምረት መመስረትና ቀጣይነት ያለው የጸጥታ ችግር እንዲሁ በዘፈቀደ የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶችና በንጹሃን ዜጎች ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን አስመልክቶ የሚደርሱ ሪፖርቶች በጣም አሳሳቢ መሆናቸውን በቃለ አቀባዩ በኩል ተገልጿል። በከፍተኛ ውጥረት ወቅት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሁኔታውን የበለጠ ሊያባብሱ ከሚችሉ ድርጊቶች ወይም ንግግሮች እንዲቆጠቡ፤ ችግሮችን በውይይት እንዲፈቱ እናሳስባለን ያለው ሪፖርቱ ወታደራዊ እርምጃ የፖለቲካ ልዩነቶችን ወይም መሰረታዊ ቅሬታዎችን አይፈታም ብሏል። በአማራ፣ በትግራይና በኦሮምያ በመንግስት ወታደሮች በርካታ ንጹሃን ዜጎች በግፍ እየተገደሉ፣ እየተፈናቀሉ ለስደት እየተዳረጉ መሆኑን ላለፉት ሰባት ዓመታት በመገናኛ ብዙሃን ሲዘገብ መቆየቱና የተባበሩት መንግስታት በጉዳዩ ዙሪያ ምንም ትኩረት አለመስጠቱ የሚታወስ ነው።

ድርቅ በአማራ ክልል

በአማራ ክልል ያለው የሰብአዊ ቀውስ እየተባባሰ መሆኑ ኗሪዎቹ እየገለጹ ነው። በተለያዩ ብዙሃን መገናኛ አውታሮች በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ አማካይነት ከስፍራው የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአገዛዙ ከሚፈጸም የጅምላ የድሮንና የከባድ መሣሪያ ጭፍጨፋ በተጨማሪ በተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች በከፍተኛ ድርቅ እየተመቱ ነው። እንስሳት የሚበሉት መኖ አጥተው እየሞቱ ነው፤ የተዘሩ ሰብሎችም ለፍሬ ሳይበቁ እየደረቁ ነው፤ ዝናብን ተስፋ አደርገው የታረሱ ማሳዎች ጦም አድረዋል። በርካታ ሰዎችም ቤታቸውን በመዝጋት ህይዎታቸውን ለማትረፍ ወደ ከተማ እየተሰደዱ ሲሆን የአገዛዙ አመራሮች “ገጽታን ያበላሻሉ” በማለት ወደ ዋና ዋና ከተሞች እንዳይገቡ በማድረግ በቀያቸው ሆነው ያለምንም እርዳታ እንዲሞቱ እየተፈረደባቸው መሆኑን ተዘግቧል። ድርቁ በአማራ ክልል በጎንደር ጠለምትና በዋግ ኽምራ ወረዳዎች ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን በአካባቢው ያሉ ኗሪዎች የተናገሩ ሲሆን በሀገሪቱ የተከሰተው ድርቅ አድማሱን በማስፋት በትግራይና በአፋርም እንስሳት እየሞቱና ኗሪውም ቀየውን ለቅቆ እየተሰደደ መሆኑ ተዘግቧል። አፋጣኝ ድጋፍ ማድረግ ካልተቻለ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ ቀውስ ሊከሰት እንደሚችል ተገልጿል። የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት መንግስት ለሚያጎርሰው ሳይሆን  በጅምላ ለሚተኩሰው የጦር መሣሪያ ትኩረት ማድረጉ አሳዛኝ ነው ሲሉ በርካታ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ያስረዳሉ።

እንቁጣጣሽ! መልካም አዲስ አመት

እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት አደረሳችሁ! የአማራ ማህበር በኦሪገን ለማህበሩ አባላትና ለመላው ኢትየጵያውያን አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ ይላል። ከአሮጌው ዘመን በመማር ለአዲሱ ዓመት አዲስ ትልም በመንደፍ ስኬት የምናሳካበት ዘመን ይሆናል ብሎ ማህበራችን ያምናል። አዲስ ዓመት አዲስ ታሪክ ለመጻፍ የተሰጠን ንጹሕ ገጽ በመሆኑ ለትውልድ የሚሻገር መልካም ስራ መስራት ተገቢ ነው። ትናንትን መለወጥ ባንችልም እንኳን፤ ነገን ግን በአዲስ ማንነትና በጠንካራ ሥራ ማሸብረቅ ዘመን ተሻጋሪ ማድረግ እንችላለን። ዘመን መለወጡ ሳይሆን ቁም ነገሩ በተለወጠው ዘመን ላይ ሁነን በአንድነት የምንሰራው ሥራ ነው ወሳኙ ነገር። አዲሱ ዓመት በህልውና ትግል ውስጥ ላለው ህዝባችን ፍትህ የሚጎናጸፍበት እንዲሆን ማህበራችን ጠንካራ ምኞቱ ነው። ለዚህም ከጠንካራ አባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር በመሆን የሰብአዊ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል። በዚህ አጋጣሚ ማህበረሰባችን በክልሉ ላሉ የድርቅ፣ የመፈናቀልና የጦርነት አደጋዎች ለተጋለጡ ወገኖች ድጋፉን እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። መልካም አዲስ አመት!   “የቀደመውን ነገር አታስቡ፤ ያለፈውን እርሱ።እነሆ፤ አዲስ ነገር አደርጋለሁ! እርሱም አሁን ይበቅላል፤ አታስተውሉትምን? በምድረ በዳም መንገድ አዘጋጃለሁ፤ በበረሓም ምንጭ አፈልቃለሁ።” ኢሳ 43፡18      

ዘመን በባተ ቁጥር ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ይነገራል። ለግንዛቤ ቀጣዩን ጽሑፍ አንብቡት።

የኢትዮጵያ ዘመን አቈጣጠር በዲያቆን ኃይለ ኢየሱስ ቢያ መስከረም  ፮ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም የዘመን አቈጣጠር ዓመታትን፣ ወራትን፣ ሳምንታትን፣ ዕለታትን፣ ደቂቃን እና ድቁቅ ሰዓታትን በየሥፍራቸው (በየመጠናቸው) የሚገልጽ፤ የሚተነትን፤ የሚለካ የቤተ ክርስቲያን የቍጥር ትምህርት ነው፡፡ እነዚህ ዅሉ ተመርምረው፣ ተመዝነው፣ ተቈጥረው ሲያበቁ ምድብና ቀመር ተሰጥቷቸው የሚገኙበትን ውሳኔና ድንጋጌ የሚያሳውቅ የዘመን አቈጣጠር – ‹ሐሳበ ዘመን› ይባላል፡፡ ዓመታት፣ ወራት፣ ሳምንታት፣ ዕለታትና ሰዓታት የሚለኩት (የሚሠፈሩት፣ የሚቈጠሩት) በሰባቱ መሥፈሪያና በሰባቱ አዕዋዳት ነው፡፡ ሰባቱ መሥፈርታት የሚባሉትም፡- ሳድሲት፣ ኃምሲት፣ ራብዒት፣ ሣልሲት፣ ካልዒት፣ ኬክሮስ እና ዕለት ሲኾኑ ሰባቱ አዕዋዳት ደግሞ፡- ዐውደ ዕለት፣ ዐውደ ወርኅ፣ ዐውደ ዓመት፣ ዐውደ ፀሐይ፣ ዐውደ አበቅቴ፣ ዐውደ ማኅተም እና ዐውደ ቀመር ናቸው፡፡ ዐውደ ዕለት – ከእሑድ እስከ ቅዳሜ ያሉት ሰባቱ ዕለታት ሲኾኑ፤ አውራኅን (ወራትን) ለማስገኘት በዚህ ሲመላለሱ ይኖራሉ፡፡ ዐውደ ወርኅ – በፀሐይ ፴ ዕለታት፣ በጨረቃ ፳፱ ወይም ፴ ዕለታት ናቸው፤ ዓመታትን ለማስገኘት በዚህ ሲመላለሱ ይኖራሉ፡፡ ዐውደ ዓመት – በፀሐይ ቀን አቈጣጠር ፫፻፷፭ ቀን ከ፲፭ ኬክሮስ፤ በጨረቃ አቈጣጠር ፫፻፶፬ ቀን ከ፳፪ ኬክሮስ ነው፡፡ እነዚህ ሦስቱ በዕለት፤ አራቱ ደግሞ...Read More

በምስራቅ አርሲ አማራንና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትን ትኩረት አድርገው በተፈፀሙ የማንነት ጥቃቶች ከ450 በላይ ንጹሓን ዜጎች መገደላቸውን ኢሰመጉ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በምስራቅ አርሲ አማራንና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትን ትኩረት አድርገው በተፈፀሙ የማንነት ጥቃቶች ከ450 በላይ ንጹሓን ዜጎች መገደላቸውን ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ። ኢሰመጉ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ አርሲ ዞን በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች በተለይ በአማራና በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችና ተቋማት ላይ በተፈፀሙ ጥቃቶች ቢያንስ 450 ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን ምክር ቤቱ ባወጣው አዲስ ሪፖርት አስታውቋል። ከመስከረም 2021 እስከ ሰኔ 2026 ባለው የምርመራ ጊዜ ውስጥ በተካተተው 158ኛው ልዩ መግለጫ ላይ፣ 37 ገጽ ያለው ሪፖርት አካላዊ ጉዳቶችን፣ የጅምላ እስራቶችን፣ አስገድዶ መድፈርንና በታጠቁ ቡድኖች የተፈፀሙ ሰፊ የንብረት ውድመትን ጨምሮ ሰፊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በማስረጃ አስደግፎ በዝርዝር አቅርቧል። ኢሰመጉ በምርመራው የአካል የመስክ ምልከታዎችንና የመረጃ አሰባሰብ መንገዶችን መጠቀሙን ገልጿል። በተጎዱት ዘጠኝ ወረዳዎች የተመዘገበው የሟቾች ቁጥርም እንደሚከተለው ነው፡- መርቲ፡ 117 ሰዎች ሼርካ፡ 116 ሰዎች ጄጁ፡ 101 ሰዎች ካባ፡ 47 ሰዎች ጉና፡ 26 ሰዎች ሆንኮሎ ዋቤ፡ 20 ሰዎች ሙኒሳ፡ 19 ሰዎች አሰኮ፡ 5 ሲቪሎችና 4 የአካባቢው ሚሊሻዎች የአርሲ አለቃ፡ 3 ሰዎች መሆናቸውን ኢሰመጉ የሟቾችን ስምና ማንነት በሪፖርቱ ውስጥ አካቷል።...Read More

በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት አስመልከቶ በአማራ ማህበር ኦሪገን የኦሪገን ሁለተኛ እንደራሴ ለሆኑት ሴናተር ጀፍ መርክሌይ ገለጻ አደረገ።

የአማራ ማህበር ኦረገን በጁን 18 ቀን 2026 ዓ.ም ከሴናተር ሮን ዋይደን ጋር ገለፃ መደረጉ ይታወቃል። በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ ለአሜሪካ የህዝብ እንደራሴዎች የማሳወቅ እንቅስቃሴውን አጠናክሮ በመቀጠል ጁን 30,2026 በኦሪገን የህዝብ እንደራሴ ለሆኑት ጀፍ መርክሌይ እየደረሰ ያለውን የአማራ ህዝብ የዘር ማጥፋት ድርጊት በመረጃ በማስደገፍ ገለጻ ተደርጓል። የአማራ ማህበር በኦሪገን የስራ አመራርና የቦርድ አባላትን እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የሚወክሉ 12 አባላት በአማራ ህዝብና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ በብልጽግናው መንግሰት እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋት ድርጊት ለማሳወቅ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አጠናክረው በመቀጠል ጁን 30 ቀን 2026 ዓ.ም ለህዝብ እንደራሴው ጀፍ መርክሌይ ገለጻ አደርገዋል። የተሰጠው መግለጫ በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የጅምላ ጭፍጨፋ፣ ግድያ፣ መፈናቀል፣ ከስራ መሰናበት፣ እገታ፣ ስደት፣ የጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና ፖለቲከኞች ያለ ፍርድ መታሰርን ያካተተ ነው። የመሰብሰብ፣ ሃሳብን በነጻነት የማራመድና የመያዝ መብት በአገዛዙ ስለመገደቡና ይህን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት በሀገሪቱ ህግ መሰረት ለማካሄድ በሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችና የህዝብ እንደራሴዎች ላይ አማራ በመሆናቸው ብቻ የዚህ መብት ተሳታፊ እንዳይሆኑ አገዛዙ የሚያደርገውን አምባገነናዊ...Read More