የስብሰባ ጥሪ

የስብሰባ ጥሪ

የአማራ ማህበር በኦሪገን አባላቱና ደጋፊዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል። እንድትገኙ በአክብሮት ይጋብዛል።

መቼ፡ October 3, 2026 @8 pm.

ቦታ፡ በዙም/zoom

መግቢያ ቃል፡ meeting ID 874 2110 7512, Pass code: 594097

  • ለአማራ ህልውና በጋራ ትግልና በማህበረሰብ አገልግሎት!
  • ህዝባችንም ከፍ ሲል ማህበረሰባችን የወደፊት ዕጣ ፈንታችን ነው።
  • የአማራ የህልውና ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ነው።

በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈጸመው ግፍ እየተባባሰና በየቀኑ በርካቶችን እያፈናቀል በመኖርና ባለመኖር ውስጥ ገብተው የወገንን ድጋፍ ይማጸናሉ። ድጋፋችን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አሁን ያስፈልጋቸዋል። ”ሊነጋ ሲል ይጨልማል” እንዲሉ አበውና እማው የነጻነታቸው ቀን እየተቃረበ ባለበት በአሁኑ ወቅት ዜጎቻችንን በርሃብና በርዛት ማጣት የሚያስቆጭ ነው የሚሆነው።

በመሆኑም አንድነታችንንና ጥንካሬያችንን በተግባር በማሳየት መደገፍ ይገባናል። ለዚህ እውንነት ደግሞ መሰባሰብና በጋራ መቆም ወሳኝ ነው።

እርስዎ  የአማራ ማህበር በኦሪገን አባል ነዎት? አባልነትዎ ማህበራችንንና ተልእኳችንን ያጠናክራልና እናመሰግናለን።

ወርሃዊ የአባልነት ክፍያዎን እየከፈሉ ነው? ቀጣይነት ያለው ድጋፍዎ ማህበሩ የበለጠ እንዲሰራ ይረዳልና አጠናክረው እንዲቀጥሉ ማህበሩ ይጠይቃል።

ለአባልነትና ድጋፍ ለማድረግ አስተባባሪዎችን ለማግኘት በዚህ ይደውሉ 9714298801

አንድነትና ትብብር የህልውና መሠረቶች ናቸው!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *