
እ.ኤ.አ. ከየካቲት 9 እስከ 15 ቀን 2026 ዓ.ም ባለው የአንድ ሳምንት ጊዜ በአማራ ፋኖ ራስን መከላከል ሃይል (ፋኖ) እና በኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ አገዛዝ የጋራ ሃይሎች መካከል በኢትዮጵያ የተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ውጊያዎች ቀጥለዋል።
በዚህ ሳምንት በአማራ ክልል በሚገኙ 11 የዞን አስተዳደሮች ከ37 በላይ ወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች የጦር ድርጊቶችና የመብት ጥሰቶች የተፈፀሙ መሆኑ ታውቋል። ዋግ ኽምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ፣ መካከለኛውና ምዕራብ ጎንደር የሚገኙበት ሲሆን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞንና በአዲስ አበባ ከተማ የተመዘገቡ ለውጦችም እንደነበሩ የአማራ ማህበር በአሜሪካ የጥናት ቡድን አረጋግጧል። በራያ ቆቦ፣ በዋድላ፣ በኤፍራታና-ግድም፣ በቀወት፣ በምንጃር – ሸንኮራ፣ በቡሬ-ዙሪያ፣ በደብረታቦር ከተማና በፎገራ ወረዳዎች ጠንከር ያሉ ውጊያዎችና የሰብአዊና ጉዳትና የንብረት ውድመት አጋጥሟል።
39ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ በሚካሄድበት ጊዜ የከተማዋ ኗሪ የሆኑ በርካታ የአማራ ወጣቶችና ተቃዋሚ የፖለቲካ ሰዎች ላይ ኢላማ ኢላማ ተደርጎ በርካቶች ታፍሰው ወደ እስር ቤት ተግዘዋል፤ አንዳንዶች ደግሞ የት እንደ ደረሱ ማወቅ እንዳልተቻለ ለማዎቅ ተችሏል። ከ12 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ከሰፈራቸውና ከስራ ገበታቸው ከአመት በፊት በጸጥታ ኃይሎች ከተወሰዱ በኋላ ደብዛቸው መጥፋቱንና በሀገሪቱ ያሉ የጸጥታ ተቋማትን ቤተሰቦች ቢያናግሩም ለምን ትጠይቃላችሁ ተብለው ከመታሰር ውጭ ያገኙት ነገር እንደሌለ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን በደብረታቦር ከተማና በፎገራ ወረዳ በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት መፈጸሙንም ማህበሩ አስታውቋል።
ሙሉ ሪፖርቱን ለማንበብ፡ https://www.amharaamerica.org/post/war-updates-from-amhara-region-ethiopia-february-9th-to-15th-2026
