ከሀገር ቤት የተላከ ደብዳቤ

ይድረስ ለልጆቼ ከአባታችሁ። እንዴው ለመሆኑ ሰላም አላችሁ? ጤንነታችሁ እንዴት ነው? እኛ ደህና ነን። እድሜ ለእናንተ ደህና ነን። እንዴው ሁኔታው ግን ያስፈራል። ግፉ በዛ። ሞት በሁሉም ቤት እየገባ ነው። የኛ ተራም እስኪደርስ ድረስ እንቆዝማለን። ለመሆኑ አማሪካ ችግር ገጠማት እንዴ? በሰልፍ ተናወጠች ብሎ እኮ የአያ ጥላሁን ልጅ በሰፊው አጫወተኝ። ይገርምሃል ትምህርቱን ከዩኒበርስቲ ተመርቆ ከተመለሰ ጊዜ ጀምሮ ስለ ውጭው እና ስለ ሀገራችን በሞባይሉ ይነግረኛል። እንዲያ እሳት የነበረ ተማሪ ኮሌጅ በጥሶ ከእኔ ከሽማግሌው ጋር ሰፈር ለሰፈር ሲውል እንዴት አንጀት ይበላል መሰለህ። የመንግስት ሹማምንት ይመጡና ውትድርና ልውሰድህ እያሉ ስለሚያስቸግሩት እነሱ መጡ በተባለ ቁጥር ጫካ ውስጥ እየዋለ እያደረ ያመልጣቸዋል። ከሰሞኑ መጥተው ቢያጡት ያን ጠንካራ ገበሬ አባቱን ካላመጣኽው እንደፋሃለን ብለውታል። አስጨናቂ ጊዜ ነው ልጆቼ። የራሳችን ጎረቤቶች ወረዳ ሂደው እየጠቆሙ ስንቱን ወጣት ወደ ውትድርና እንዲጋዝ አደረጉት መሰለህ። የእኔ ነገር ለመሆኑ ምን ይፈጠር ብላችሁ ነው በአማሪካ ላይ ሰልፍ የወጣችሁት። ሰው በሃገሩ ስንት ግፍ እየደረሰበት ተሸክሞ ዝም ብሎ የለም እንዴ! መቼም ያልታደለ አማራ ይውጣ አልተባለም አይደል? መቼም የእኛ ጉደኞች እንደሚያደርጉት...Read More