Blog

A reminder, Saturday 14th of February 2026

Amhara Association Of Oregon is inviting you to a scheduled Zoom meeting. Topic: General  conference Time: Feb 14, 2026 08:00 PM Pacific Time (US and Canada) Join Zoom Meeting https://us06web.zoom.us/j/81548770702?pwd=xN3RTgrrXufVYRvS9uikvnOl1bZW5X.1 Meeting ID: 815 4877 0702 Passcode: 134457 --- One tap mobile +13462487799,,81548770702#,,,,*134457# US (Houston) +16694449171,,81548770702#,,,,*134457# US Join instructions https://us06web.zoom.us/meetings/81548770702/invitations?signature=EFkS87OTVN2MHEZUlT2y88QcMnlco0hhfKL_VVwK7Hc

እንኳን ለዐቢይ ጾምና ለሮመዳን ጾም አደረሳችሁ

በዚህ ሳምንት የሁለት አበይት አብያተ ዕምነቶች ሁለት ታላላቅ ጾሞች ተከታትለው ይጀመራሉ። ሰኞ የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን የሚጀምሩት ሊቀ ካህን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾሞ አማንያን ይጾሙት ዘንድ የተሰጠው ዐቢይ ጾም ወይም የሆዳዴ ጾም ይጀምራል። ከሁለት ቀን በኋላ ረቡዕ የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ደግሞ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚጾሙት የታላቁ የሮመዳን ጾም ይጀመራል። በኦሪገን የአማራ ማህበር እንኳን ለጾሙ በሰላም አደረሳችሁ ይላል። ነቢዩ ኢሳይያስ (58፤6-7) በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ስለጾም እንዲህ ይላል። “እኔስ የመረጥኩት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፣ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፤ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፣ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን? እንጀራህንስ ለተራበ ትቆርስ ዘንድ፣ ስደተኞችንና ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፣ የተራቆቱትንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፣ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሸግ አይደለምን?” ወንጌለኛው ቅዱስ ማቲዎስም (25፤35) ጾማችን ከጠብና ከሙግት በመራቅ ብቻ ሳይሆን መልካም ነገር በመስራት መሆን እንዳለበት የዓለም ቤዛ ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ያሰተማረውን እንዲህ ያዘክራል። “ተርቤ፣ አብልታችሁኛልና፣ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛል፣ እንግዳ ሁኜ ተቀብላችሁኛልና፣ ታርዤ አልብሳችሁልኛልና፣ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፣ ታስሬ ወደ እኔ...Read More

ሰምተዋል?

ሰምተዋል? በኦሪገን የአማራ ማህበር አጠቃላይ ስብሰባ በመጪው ቅዳሜ በኦን ላይን መጥራቱን? ከቤትዎ ሁነው በእጅ ሞባይልዎ ወይም በሚመችዎ የመገናኛ መሣሪያ በመጠቀም ስብሰባውን ይታደሙ። አደራ እንዳይቀሩ። ማህበርዎን ያጠናክሩ! አንድነት ኃይል ነው!

የአገዛዙ የግፍ ግድያ ባህር ዳር ከተማ!

በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ እየፈፀመ ያለው አገዛዝ ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸውን የሕክምና ዶክተሮችን፣ የነቁ አማራዎችንና ባለሐብቶችን በየቀኑ ከቤታቸው እየተጎተተ እያወጣ ማረዱን ቀጥሏል:: በመሆኑም ትላንት በቀን 26/05/2018ዓ.ም ዶ/ር ፀጋሁን ስሜ የሚባልን በምሥራቅ ጎጃም፣ የደብረወርቅ ተወላጅና የባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ነዋሪ እንዲሁም የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሠራተኛ የነበረውን ጥዋት ሥራ ለመግባት በጉዞ ላይ እያለ በአገዛዙ ወታደሮች ይያዛል። የአገዛዙ ወታደሮች ከያዙት በሗላ ወደ ቤቱ መልሰው በመውሰድ በቤቱ ፍተሻ ያደርጋሉ። ቤቱን በመፈተሽ ምንም ነገር ያላገኙት ወታደሮች ዶ/ር ፀጋሁንን ወደ ቤዛዊት ቤተመንግሥት አካባቢ ወስደው ገድለው ጥለውታል። የአገዛዙ ወታደሮች ዶ/ር ፀጋሁንን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉ በሗላ በማን አለብኝነት በራሱ ስልክ ለባለቤቱ በመደወል አስከሬኑን እንድትወስድ ይነግሯታል:: ዶ/ር ፀጋሁንን ምን እንዳነጋገሩት ባይታወቅም ከሳምንት በፊት የአማራ ክልል ጤና ቢሮው ኃላፊ የሆነው አብዱልከሪም መንግሥቱ ለብቻው ቢሮ እንዳነጋገረውና ከቢሮ ሲወጣም ጥሩ ስሜት እንዳልነበረው ጓደኞቹ ይናገራሉ:: ቤቱ ሲፈተሽም ምንም አይነት መረጃ እንዳልተገኘና የአገዛዙ ወታደሮችም የወሰዱት ማስረጃ እንደሌለ የዶ/ር ፀጋሁን ቤተሰቦች አረጋግጠዋል። በክልሉ ዋና ከተማ በባህር ዳር እንዲህ አይነት አሰቃቂ ግድያዎች...Read More

Great Ethiopian Renaissance Dam (GERD)

Barbados' Prime Minister, Mia Mottley testimony on GERD with Trevor Nooah [video width="1920" height="1080" mp4="http://oregonamhara.org/wp-content/uploads/2026/02/GERD.mp4"][/video]

እንኳን ለከተራና ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በኦሪገንና በመላው ዓለም ለምትኖሩ የክረስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ2018 ዓ.ም ለኢየሱስ ክርስቶስ የከተራና የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት በኦሪገን የአማራ ማህበር መልካም ምኞቱን ይገልጻል። እስራኤላውያን ዮርዳኖስን በከተራው እንደተሻገሩት ሁሉ ሀገራችንም ወደ ተሟላ ሰላም የምትሻገርበት ጊዜ ይሁንልን። በጥምቀቱም ሰላምን፣ ፍቅርን አንድነትንና ለሰው ልጅ ትህትና የምናሳይበት እንዲሆን የአማራ ማህበር በኦሪገን ምኞቱን ይገልጻል። በዓሉን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖቻችንን እያሰብን እንዲሆን ማህበሩ ማሳሰብ ይወዳል። መልካም በዓል!

የአማራ ዜጎች ግድያ፣ መፈናቀል፣ እስራትና እገታ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ከታህሳስ 29፣ 2025 እስከ ጥር 4፣ 2026 ባለው የሳምንት ጊዜ ውስጥ በአማራ ፋኖ ራስን የመከላከል ኃይል (ፋኖ) እና በኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ አገዛዝ መካከል በተደረጉ ውጊያዎች ከ34 በላይ በሆኑ የአማራ ክልል ወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የአማራ ማህበር በአሜሪካ (AAA) በአወጣው ሳምንታዊ ጥናት አስታውቋል። ኢሰብአዊ ድርጊቱ የተፈጸመው በክልሉ ከሚገኙት የአስተዳደር መዋቅሮች ከኦሮሞ ልዩ ዞን ውጪ በሁሉም አካባቢዎች ነው። በተለይም ደግሞ በራያ ባላ፣ በቡግና፣ በስናን፣ በአዋበል፣ በአየሁ ጓጉሳ እና በምዕራብ ደምቢያ ወረዳዎች ሰላማዊ ሰዎች መጎዳታቸውን ጥናቱ አመላክቷል። በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ በአማራ ማህበረሰብ ላይ ጉዳት መድረሱም ተገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ወከባ፣ እስራትና የመፈናቀል ሥራዎች መቀጠላቸውን ጥናቱ ያሳያል። በአማራ ክልል በሚገኙ 3 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ የድሮን እንቅስቃሴ ተመዝግቧል። እነዚህም በምስራቅ ጎጃም ፣በምዕራብ ጎጃም እና በሰሜን ጎጃም ዞኖች ውስጥ የሚገኙትን የስናን፣ ጃቢ-ጠህናን እና የጎንጂ ቆለላ ወረዳዎችን ያጠቃልላል። በሁለቱ ክስተቶች የዜጎች ጉዳት ደርሷል። በአማራ ክልል በኮረም፣ በራያ ቆቦ፣ በአምባሰል፣ በሀብሩ እና በወምበርማ ወረዳዎች የሰላማዊ ሰዎች...Read More

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

የአማራ ማህበር በኦሪገን ለመላው አባላቱና ለእምነቱ ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልጻል። በዓሉን ስናከብር በብዙ መጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥በርሃብና በመታረዝ ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን እያሰብን መሆን ይኖርበታል። በሀገራችን በተለይም ደግሞ በአማራው ህዝብ ላይ እየደረሰ ባለው ኢሰብአዊ ድርጊት የተነሳ በስደት፣ በመጠለያ እንዲሁም በየቤታቸው ሁነውም በተከሰተው የኑሮ ውድነት ምክንያት ቤታቸው የሚበላም፣ የሚጠጣና የሚለበስ ያጡትን ወገኖቻችን በማሰብ መሆን ይኖርበታል። እንዲያ ሲሆን ለሰው ልጅ ደኅነት የተወለደው ክርስቶስ መታሰቢያ በዓል የተሟላ ያደርገዋል። በክርስቶስ መወለድ ‘’በጨለማ የሚኖር ህዝብ ብርሃን አየ” እንደተባለው ሁሉ በመፈናቀል፣ በጦርነትና በኑሮ ውድነት ምክንያት በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችንን በማሰብና የምንችለውን በማድረግ እንዲሆን ማህበሩ ማስታወስ ይፈልጋል። የገና በዓል የአንድነትና የፍቅር በዓልም ነው። ቤተሰብ እስከ ጎረቤት አብረው በደስታ የሚያከብሩት እንደ መሆኑ መጠን በአንድነትና በፍቅር በመሆን በችግር ውስጥ ያለው ህዝባችን ሰላም አግኝቶ፣ ራሱን ችሎ ከችግር ወጥቶ የሚኖርበት ዘመን እንዲመጣ በጋራ መቆም ይጠበቅብናል። በሀገረ አሜሪካ የሚኖሩ ልጆቻችን የአማራን ባህልና ቱፊት ማሳወቅና ማስተማርም ይጠበቅብናል። በገና ጨዋታ አይቆጡም...Read More

DHS ለኢትዮጵያ ጊዜያዊ ጥበቃ መቋረጡን አስታውቋል

ዋሽንግተን - የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያውያን ሰጥቶት የነበረውን ጊዜያዊ ጥበቃ ማቋረጡን የሀገር ውስጥ ደህንነት ዋና ፀሐፊ ክሪስቲ ኖኤም ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። አሁን ያለው የሀገሪቱ ጊዜያዊ ሁኔታ ​​ለTPS የተቀመጠውን ህጋዊ መስፈርቶችን የማያሟላ በመሆኑና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሁኔታዎች ከአሁን በኋላ ለሚመለሱት የኢትዮጵያ ዜጎች የግል ደህንነት ከባድ ስጋት ስለማይፈጥር ነው የተቋረጠው ብለዋል ኖኤም። በዩናይትድ ስቴትስ ለመቆየት ሌላ ህጋዊ መሰረት የሌላቸው ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በፈቃደኝነት ከዩናይትድ ስቴትስ ለመውጣት 60 ቀናት ተሰጥቷቸዋል። በፈቃደኝነት ሚወጡ ኢትዮጵውያን ነጻ የአውሮፕላን ትኬትና 1000 ዶላር ጉርሻ ይሰጣቸዋል ብለዋል ዋና ጸሐፊዋ። ከዚህም በተጨማሪም ህጋዊ የኢሚግሬሽን እድሎችንም ያካተተ ነው። ይሁን እንጅ ከየካቲት 13 ቀን 2026 ዓ.ም በኋላ የሀገር ውስጥ ደህንነት መምሪያ የTPS አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያለ ምንም ቅደመ ሁኔታ ማሰር እና ማባረር ከመቻሉም በላይ ወደ አሜሪካ ተመልሰው እንዲገቡ ፈጽሞ እንደማይፈቀድላቸው ከመግለጫው ለመረዳት ተችሏል።   https://www.uscis.gov/newsroom/news-releases/dhs-announces-the-termination-of-temporary-protected-status-for-ethiopia