Blog

War updates from Amhara Region, Ethiopia – February 16th to 22nd, 2026

Overview   For the week of February 16th to 22nd, 2026, fighting between the Amhara Fano self-defense force (Fano) and Oromo Prosperity Party regime joint forces (regime forces) has continued in various parts of Amhara Region in Ethiopia.   This week battle events and rights violations were recorded in more than 36 woreda/city administrations across 10 zonal administrations in Amhara Region. These zones included Wag-Hemra, North Wollo, South Wollo, North Shewa, East Gojjam, West Gojjam, North Gojjam, South Gonder, Central Gonder and West Gonder Zones.   Civilian casualties were recorded in 15 woreda/city administrations across 7 zonal administrations in Amhara Region. These included Gubalafto, Mekdela, Wegdi, Efratana-Gidim, Minjar-Shenkora, Kewet, Antsokiyana-Gemza, Gozamin, Finote-Selam, Jabi-Tehnan, Wemberima, Quarit, North Mecha, Bahir-Dar-Zuriya and Alefa Woredas in North Wollo, South Wollo, North Shewa, East Gojjam, West Gojjam, North Gojjam and Central Gonder Zones.   Arrests were recorded in Kobo City and Raya-Alamata Woredas of North...Read More

የአድዋ ድል ታሪክ

የአድዋ ጦርነት በየካቲት ፳፫ ቀን ፲፰፻፹፰ ዓ.ም. በኢትዮጵያና ኢጣሊያ መካከል የተካሄደ ውጊያ ሲሆን የአንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነት ክፍል ነው። በኢትዮጵያ አሸናፊነት የጣልያን የቀኝ ግዛት ማስፋፋት ተኮላሸ። ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ ' ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ፤ ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ መድፍ አገላባጭ ብቻለብቻ፤ የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው፤ የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኅተም፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል ነው፡፡ የመላው ዓለም ተፈጥሮአዊ ግብር እና ሰብአዊ ክብር የታደሠው፤ በእውነትና በፍትህ ህልውናና ምልዓት ላይ የተሰካ ትልቅ ጥርስ የተነቀለው … በአድዋ የታላቅ ህዝቦች ታላቅ ድል ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ስንሄድ 1066 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ታላቁ ጦርነት የተደረገበትና ታላቁ ድል የተገኘበት ሥፍራ አድዋ ከተማና የከተማው ግድም ገመገሞች ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያውያን አቡሻኽር (Julian calendar) የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም፤ ወይም በአውሮጳውያን የዘመን አቆጣጠር (Gregorian Calendar) February (የካቲት) መጨረሻ እና March (መጋቢት) መጀመሪያ ላይ 1896. ለጦርነቱ መነሻ የሆነው ውል የተፈፀመው በዚሁ ዘመን ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 468 ኪሎ ሜትር ርቀት ግድም ከውጫሌ ከተማ ግርጌ ከአምባሰል ተራራ ሥር...Read More

አድዋ

[video width="1920" height="1080" mp4="http://oregonamhara.org/wp-content/uploads/2026/02/Tamir-adawa-walk-and-talk.mp4"][/video]

አድዋ!

የአድዋ ጦርነት የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ኢትዮጵያውያን በዐፄ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ ብሩር መሪነት ጣሊያንን በአድዋ ያሸነፉበት ታሪካዊ ድል ነው። ጦርነቱ የመጣው ጣሊያን በውል ንግግር (ውጫሌ ውል አንቀጽ 17) ሰበብ ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ለመያዝ ሙከራ በማድረጓ ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያን በፅናት በመዋጋት የቅኝ አገዛዝ ሙከራውን አክሽፈውታል።   የአድዋ ጦርነት ዋና ዋና ነጥቦች፦ የጦርነቱ መንስኤ፦የውጫሌ ውል አለመግባባት፣ ጣሊያን አጠቃላይ ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ያደረገችው ህገ-ወጥ ጥረት። መሪዎች፦ዐፄ ምኒልክ፣ እቴጌ ጣይቱ፣ ራስ መኮንን፣ ራስ አሉላ፣ ራስ ਮੰገሻ እና ሌሎችም በጋራ ተዋግተዋል። የድል ቀን፦የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም (March 1, 1896)። ውጤት፦ጣሊያን በከፍተኛ ሁኔታ ተሸንፋ የ«ውጫሌ ውል»ን በመሰረዝ የኢትዮጵያን ነፃነት አምናለች። ታሪካዊ ፋይዳ፦ጥቁር ህዝቦች በነጮች ቅኝ ገዢዎች ላይ የተቀዳጁት የመጀመሪያው ትልቅ ድል በመሆኑ፣ ለታላቁ የአፍሪካ አንድነት እና ለቀለም አቀፍ ትግል ትልቅ ስንቅ ሆኗል።

ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ (አባ ታጠቅ) ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ

ጀግናዉ ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ (ጥር ፮ ቀን ፲፰፻፲፩ ዓ.ም. እስከ  ሚያዝያ ፮ ቀን፲፰፻፷ ዓ.ም.) ከ፲፰፻፵፯ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታችው ድረስ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። በትውልድ ስማቸው ካሳ ኀይሉ ሲባሉ፣ በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ፣ በወታደራዊ ስማቸው መይሳው ካሳና እንዲሁም አንድ ለናቱ ተብለው የሚታወቁ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ወታደርና ፖለቲከኛ ነበሩ። ቴዎድሮስ ጥር ፮ ቀን ፲፰፻፲፩ ዓ.ም. ሻርጌ በተባለ ቦታ ቋራ  ውስጥ፣ ከጎንደር ከተማ በስተ ምዕራብ ተወለዱ። የተወለዱትም አገሪቷ በባላባቶች ተከፋፍላ በምትመራበት-ዘመነ መሳፍንት በሚባለው ወቅት ነበር። አባታቸው ደጃዝማች ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ የቋራ ገዢ ነበሩ። ዓፄ ቴዎድሮስ በህጻንነታቸው የቄስ ትምህርት ከቀሰሙ በኋላ፣ የአጎታቸውንና በኋላም ለጥቂት ጊዜ የጎጃሙን ጦር መሪ የጎሹ ዘውዴን ጦር ተቀላቀሉ። በዚሁ የውትድርና ዘመናቸው ከፍተኛ ችሎታን ማስመዝገብ ስለጀመሩና ዝናቸው ስለተስፋፋ በ፲፰፻፴፱ ዓ.ም. በወይዘሮ መነን ሊበን አምዴ አነሳሽነት የልጇን የራስ አሊ አሉላን ልጅ፣ ተዋበች አሊን አገቡ፤ እንዲሁም በደጃዝማችነት ማዕረግ የቋራ አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ። ቴዎድሮስ ግን በ፲፰፻፵፬ ዓ.ም. አጠቃላይ የዘመነ መሳፍንት ሥርዓትን በመቃወም በሰሜናዊ ባላባቶች ላይ ዘመቻ ጀመሩ። በተከታታይ ዘመቻወች የገጠሟቸውን ባላባቶች ስላሸነፉ፣ መጀመሪያ የራስ ማዕረግን በኋላም የንጉሥ ማዕረግን በአንድ ዓመት ውስጥ ተቀዳጁ። በየጊዜው በሚያደርጉት የተሳካ ዘመቻ የዘመኑን ባላባቶች ኃይል በመሰባበር የካቲት ፫ ቀን ፲፰፻፵፯ ዓ.ም ንጉሥ ካሳ - ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ተብለው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆኑ። ሥርዓተ ንግሡ...Read More

በአማራ ክልል ከየካቲት 9 እስከ 15፣ 2026 ዓ.ም ጊዜ ውስጥ የተፈጸሙ ሰብአዊ ጥቃቶች

እ.ኤ.አ. ከየካቲት 9 እስከ 15 ቀን 2026 ዓ.ም ባለው የአንድ ሳምንት ጊዜ በአማራ ፋኖ ራስን መከላከል ሃይል (ፋኖ) እና በኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ አገዛዝ የጋራ ሃይሎች መካከል በኢትዮጵያ የተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ውጊያዎች ቀጥለዋል። በዚህ ሳምንት በአማራ ክልል በሚገኙ 11 የዞን አስተዳደሮች ከ37 በላይ ወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች  የጦር ድርጊቶችና የመብት ጥሰቶች የተፈፀሙ መሆኑ ታውቋል። ዋግ ኽምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ፣ መካከለኛውና ምዕራብ ጎንደር የሚገኙበት ሲሆን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞንና በአዲስ አበባ ከተማ የተመዘገቡ ለውጦችም እንደነበሩ የአማራ ማህበር በአሜሪካ የጥናት ቡድን አረጋግጧል። በራያ ቆቦ፣ በዋድላ፣ በኤፍራታና-ግድም፣ በቀወት፣ በምንጃር - ሸንኮራ፣ በቡሬ-ዙሪያ፣ በደብረታቦር ከተማና በፎገራ ወረዳዎች ጠንከር ያሉ ውጊያዎችና የሰብአዊና ጉዳትና የንብረት ውድመት አጋጥሟል። 39ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ በሚካሄድበት ጊዜ የከተማዋ ኗሪ የሆኑ በርካታ የአማራ ወጣቶችና ተቃዋሚ የፖለቲካ ሰዎች ላይ ኢላማ ኢላማ ተደርጎ በርካቶች ታፍሰው ወደ እስር ቤት ተግዘዋል፤ አንዳንዶች ደግሞ የት እንደ ደረሱ ማወቅ እንዳልተቻለ ለማዎቅ ተችሏል። ከ12 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ከሰፈራቸውና ከስራ ገበታቸው...Read More

የአማራን አንድነት ማጠናከር አንገብጋቢ ጉዳይ ነው

አንድነታችን ማጠናከር ወቅቱ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው ሲሉ በኦሪገን የአማራ ተወላጆች ገለጹ። በኦሪገን የአማራ ማህበር አጠቃላይ ስብሰባ ላይ አባላቱ እንደገለጹት በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብአዊ ቀውስ በሚቻለው መጠን ለመደገፍም ሆነ ለዓለም ድምጽ ለማሰማት በጋራ መቆም ወሳኝ መሆኑ በአጽንኦት አባላቱ ገልጸዋል። በ2025 ዓ.ም ማህበሩ በርካታ ስራዎችን መስራቱን በቀረበው ሪፖርት ለማወቅ ተችሏል። ከተሰሩ ስራዎች መካከልም በአገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ ለኦሪገን መንግስትና ለፌዴራል መንግስቱ የህዝብ እንደራሴዎች ተገቢው መረጃ እንዲደርሳቸው ተደርጓል። ከዚህም በተጨማሪ ለተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ የሚውል የገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ ተሰርቷል። የአባላት ቁርጠኝነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የማህበሩ አመራር የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ለማሰባሰብ ተሞክሯል። ይሁን እንጂ ጊዜን ሰጥቶ በቁርጠኝነት የመሰባሰብና የሚጠበቀውን ያህል አስተዋጽኦ ማድረግ አልተቻለም። አባላቱ በበኩላቸው የመረጃ ክፍተቶች እንደነበሩ ጠቁመው ይህን ክፍተት በማረም አጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን ትኩረት ተሰጥቶታል። በመንግስት እየተመራ በአማራ ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እየተከታተሉ ለአባላቱ፣ ለተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና ድርጅቶች፣ ለአሜሪካ ባለስልጣናት በማሳወቅ፣ የምናገኘውን ሚዲያ በመጠቀም ድምጻችንን በማሰማት ግፉ ፍጻሜ እንዲደርስና የአማራ ህዘብ ህልውና እንዲረጋገጥ በትጋት እንደሚሰራ አጽንኦት ተሰጥቶታል። የአማራ...Read More