Day: February 21, 2026
ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ (አባ ታጠቅ) ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
ጀግናዉ ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ (ጥር ፮ ቀን ፲፰፻፲፩ ዓ.ም. እስከ ሚያዝያ ፮ ቀን፲፰፻፷ ዓ.ም.) ከ፲፰፻፵፯ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታችው ድረስ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። በትውልድ ስማቸው ካሳ ኀይሉ ሲባሉ፣ በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ፣ በወታደራዊ ስማቸው መይሳው ካሳና እንዲሁም አንድ ለናቱ ተብለው የሚታወቁ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ወታደርና ፖለቲከኛ ነበሩ። ቴዎድሮስ ጥር ፮ ቀን ፲፰፻፲፩ ዓ.ም. ሻርጌ በተባለ ቦታ ቋራ ውስጥ፣ ከጎንደር ከተማ በስተ ምዕራብ ተወለዱ። የተወለዱትም አገሪቷ በባላባቶች ተከፋፍላ በምትመራበት-ዘመነ መሳፍንት በሚባለው ወቅት ነበር። አባታቸው ደጃዝማች ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ የቋራ ገዢ ነበሩ። ዓፄ ቴዎድሮስ በህጻንነታቸው የቄስ ትምህርት ከቀሰሙ በኋላ፣ የአጎታቸውንና በኋላም ለጥቂት ጊዜ የጎጃሙን ጦር መሪ የጎሹ ዘውዴን ጦር ተቀላቀሉ። በዚሁ የውትድርና ዘመናቸው ከፍተኛ ችሎታን ማስመዝገብ ስለጀመሩና ዝናቸው ስለተስፋፋ በ፲፰፻፴፱ ዓ.ም. በወይዘሮ መነን ሊበን አምዴ አነሳሽነት የልጇን የራስ አሊ አሉላን ልጅ፣ ተዋበች አሊን አገቡ፤ እንዲሁም በደጃዝማችነት ማዕረግ የቋራ አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ። ቴዎድሮስ ግን በ፲፰፻፵፬ ዓ.ም. አጠቃላይ የዘመነ መሳፍንት ሥርዓትን በመቃወም በሰሜናዊ ባላባቶች ላይ ዘመቻ ጀመሩ። በተከታታይ ዘመቻወች የገጠሟቸውን ባላባቶች ስላሸነፉ፣ መጀመሪያ የራስ ማዕረግን በኋላም የንጉሥ ማዕረግን በአንድ ዓመት ውስጥ ተቀዳጁ። በየጊዜው በሚያደርጉት የተሳካ ዘመቻ የዘመኑን ባላባቶች ኃይል በመሰባበር የካቲት ፫ ቀን ፲፰፻፵፯ ዓ.ም ንጉሥ ካሳ - ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ተብለው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆኑ። ሥርዓተ ንግሡ...Read More
በአማራ ክልል ከየካቲት 9 እስከ 15፣ 2026 ዓ.ም ጊዜ ውስጥ የተፈጸሙ ሰብአዊ ጥቃቶች
እ.ኤ.አ. ከየካቲት 9 እስከ 15 ቀን 2026 ዓ.ም ባለው የአንድ ሳምንት ጊዜ በአማራ ፋኖ ራስን መከላከል ሃይል (ፋኖ) እና በኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ አገዛዝ የጋራ ሃይሎች መካከል በኢትዮጵያ የተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ውጊያዎች ቀጥለዋል። በዚህ ሳምንት በአማራ ክልል በሚገኙ 11 የዞን አስተዳደሮች ከ37 በላይ ወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች የጦር ድርጊቶችና የመብት ጥሰቶች የተፈፀሙ መሆኑ ታውቋል። ዋግ ኽምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ፣ መካከለኛውና ምዕራብ ጎንደር የሚገኙበት ሲሆን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞንና በአዲስ አበባ ከተማ የተመዘገቡ ለውጦችም እንደነበሩ የአማራ ማህበር በአሜሪካ የጥናት ቡድን አረጋግጧል። በራያ ቆቦ፣ በዋድላ፣ በኤፍራታና-ግድም፣ በቀወት፣ በምንጃር - ሸንኮራ፣ በቡሬ-ዙሪያ፣ በደብረታቦር ከተማና በፎገራ ወረዳዎች ጠንከር ያሉ ውጊያዎችና የሰብአዊና ጉዳትና የንብረት ውድመት አጋጥሟል። 39ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ በሚካሄድበት ጊዜ የከተማዋ ኗሪ የሆኑ በርካታ የአማራ ወጣቶችና ተቃዋሚ የፖለቲካ ሰዎች ላይ ኢላማ ኢላማ ተደርጎ በርካቶች ታፍሰው ወደ እስር ቤት ተግዘዋል፤ አንዳንዶች ደግሞ የት እንደ ደረሱ ማወቅ እንዳልተቻለ ለማዎቅ ተችሏል። ከ12 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ከሰፈራቸውና ከስራ ገበታቸው...Read More
