እንኳን ለዐቢይ ጾምና ለሮመዳን ጾም አደረሳችሁ

በዚህ ሳምንት የሁለት አበይት አብያተ ዕምነቶች ሁለት ታላላቅ ጾሞች ተከታትለው ይጀመራሉ። ሰኞ የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን የሚጀምሩት ሊቀ ካህን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾሞ አማንያን ይጾሙት ዘንድ የተሰጠው ዐቢይ ጾም ወይም የሆዳዴ ጾም ይጀምራል። ከሁለት ቀን በኋላ ረቡዕ የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ደግሞ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚጾሙት የታላቁ የሮመዳን ጾም ይጀመራል። በኦሪገን የአማራ ማህበር እንኳን ለጾሙ በሰላም አደረሳችሁ ይላል። ነቢዩ ኢሳይያስ (58፤6-7) በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ስለጾም እንዲህ ይላል። “እኔስ የመረጥኩት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፣ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፤ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፣ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን? እንጀራህንስ ለተራበ ትቆርስ ዘንድ፣ ስደተኞችንና ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፣ የተራቆቱትንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፣ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሸግ አይደለምን?” ወንጌለኛው ቅዱስ ማቲዎስም (25፤35) ጾማችን ከጠብና ከሙግት በመራቅ ብቻ ሳይሆን መልካም ነገር በመስራት መሆን እንዳለበት የዓለም ቤዛ ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ያሰተማረውን እንዲህ ያዘክራል። “ተርቤ፣ አብልታችሁኛልና፣ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛል፣ እንግዳ ሁኜ ተቀብላችሁኛልና፣ ታርዤ አልብሳችሁልኛልና፣ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፣ ታስሬ ወደ እኔ...Read More