የአገዛዙ የግፍ ግድያ ባህር ዳር ከተማ!

በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ እየፈፀመ ያለው አገዛዝ ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸውን የሕክምና ዶክተሮችን፣ የነቁ አማራዎችንና ባለሐብቶችን በየቀኑ ከቤታቸው እየተጎተተ እያወጣ ማረዱን ቀጥሏል:: በመሆኑም ትላንት በቀን 26/05/2018ዓ.ም ዶ/ር ፀጋሁን ስሜ የሚባልን በምሥራቅ ጎጃም፣ የደብረወርቅ ተወላጅና የባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ነዋሪ እንዲሁም የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሠራተኛ የነበረውን ጥዋት ሥራ ለመግባት በጉዞ ላይ እያለ በአገዛዙ ወታደሮች ይያዛል። የአገዛዙ ወታደሮች ከያዙት በሗላ ወደ ቤቱ መልሰው በመውሰድ በቤቱ ፍተሻ ያደርጋሉ። ቤቱን በመፈተሽ ምንም ነገር ያላገኙት ወታደሮች ዶ/ር ፀጋሁንን ወደ ቤዛዊት ቤተመንግሥት አካባቢ ወስደው ገድለው ጥለውታል።
የአገዛዙ ወታደሮች ዶ/ር ፀጋሁንን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉ በሗላ በማን አለብኝነት በራሱ ስልክ ለባለቤቱ በመደወል አስከሬኑን እንድትወስድ ይነግሯታል::
ዶ/ር ፀጋሁንን ምን እንዳነጋገሩት ባይታወቅም ከሳምንት በፊት የአማራ ክልል ጤና ቢሮው ኃላፊ የሆነው አብዱልከሪም መንግሥቱ ለብቻው ቢሮ እንዳነጋገረውና ከቢሮ ሲወጣም ጥሩ ስሜት እንዳልነበረው ጓደኞቹ ይናገራሉ:: ቤቱ ሲፈተሽም ምንም አይነት መረጃ እንዳልተገኘና የአገዛዙ ወታደሮችም የወሰዱት ማስረጃ እንደሌለ የዶ/ር ፀጋሁን ቤተሰቦች አረጋግጠዋል። በክልሉ ዋና ከተማ በባህር ዳር እንዲህ አይነት አሰቃቂ ግድያዎች ሲፈጸሙ ባለፈው ዓመት ከተገደሉት ከዶ/ር አንዷለም ቀጥሎ በአንድ አመት ውስጥ ዶ/ር ጸጋሁን ሁለተኛው ሲሆኑ አገዛዙ የአማራ ህዝብን በሙያቸው የሚያገለግሉ ባለሙያዎችን ለማጥፋትና ሰብአዊ ቀውስ ለመፍጠር ያለውን ቁርጠኝነት ማሳያ ነው። ባለፉት ሦስት ዓመታት በርካታ ሀኪሞች ታስረዋል፣ ተንገላተዋል፣ የደህንነት ዋስትና ስላጡ ባህር ዳርን እና አማራ ክልልን ለቀው ወደሌላ አካባቢዎች በተለይም ወደ አዲስ አበባ ፈልሰዋል።
ለዶ/ር ፀጋሁን ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን እንመኛለን

 

ምንጭ፡ ኢትዮ ሰገነት ሚዲያ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *