
በኦሪገንና በመላው ዓለም ለምትኖሩ የክረስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ2018 ዓ.ም ለኢየሱስ ክርስቶስ የከተራና የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት በኦሪገን የአማራ ማህበር መልካም ምኞቱን ይገልጻል። እስራኤላውያን ዮርዳኖስን በከተራው እንደተሻገሩት ሁሉ ሀገራችንም ወደ ተሟላ ሰላም የምትሻገርበት ጊዜ ይሁንልን። በጥምቀቱም ሰላምን፣ ፍቅርን አንድነትንና ለሰው ልጅ ትህትና የምናሳይበት እንዲሆን የአማራ ማህበር በኦሪገን ምኞቱን ይገልጻል። በዓሉን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖቻችንን እያሰብን እንዲሆን ማህበሩ ማሳሰብ ይወዳል።
መልካም በዓል!

