ለኦሪገን የአማራ ማህበር አባላትና አባል ላልሆናችሁ ወገኖች በሙሉ፣ በቅርቡ በአዲስ መልክ የተዋቀረው የማህበራችን የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት በጥሩ መንፈስና ትብብር ማህበራችንን በእግሩ ለማቆም እየተንቀሳቀስን ሲሆን በተጓዳኝም በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ በተፈጠረው ዘርን ያማከል የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ማፍረስና ማፈናቀል፣ጦርነትና ድርቅ ምክንያት እጅግ በጣም ብዙ ወገኖቻችን ለከፋ ርሀብ፣ በሽታና እርዛት ተጋልጠው አስፈሪ የህልውና አደጋ ውስጥ በመሆናቸው እነዚህን ወገኖች አቅማችን በሚፈቅደው መጠን ለማገዝ ይረዳን ዘንድ በቅርቡ ተግባራዊ የሚሆን ሀብት የማሰባሰብ ስራ (fund raising) አቅደን በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ ነን። በወገናችን ላይ እየደረሰ ያለውን አሰቃቂ መከራ በተለያዩ የብዙሀን መገናኛ አውታሮች እያየንና እየሰማን ነው። እነዚህ ችግሮች የህሊና እረፍት የነሷችሁና በገንዘብ ወገናችሁን መርዳት ለምትፈልጉ የማህበራችንን የባንክ ሂሳብ ቁጥር በሚከተለው መልኩ አስቀምጠንላችኋል። Chase bank Account #: 528321659 Routing #: 325070760 በ Zelle ገንዘብ መርዳት ለምትፈልጉ : accounting@oregonamhara.org በ Venmo ገንዘብ መርዳት ለምትፈልጉ : @AmharaAssociationOR በ CashApp ገንዘብ መርዳት ለምትፈልጉ : $AmharaAssociationOR በ PayPal ገንዘብ መርዳት ለምትፈልጉ ከታች ያለውን ምልክት ይጫኑ : ለበለጠ መረጃና ጥያቄዎች ፣ እየደወላችሁ ማነጋገር ተችላላችሁ። 1) ደረጀ….503-740-7328 2) ጥላሁን…971-506-9839