DHS ለኢትዮጵያ ጊዜያዊ ጥበቃ መቋረጡን አስታውቋል
ዋሽንግተን - የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያውያን ሰጥቶት የነበረውን ጊዜያዊ ጥበቃ ማቋረጡን የሀገር ውስጥ ደህንነት ዋና ፀሐፊ ክሪስቲ ኖኤም ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። አሁን ያለው የሀገሪቱ ጊዜያዊ ሁኔታ ለTPS የተቀመጠውን ህጋዊ መስፈርቶችን የማያሟላ በመሆኑና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሁኔታዎች ከአሁን በኋላ ለሚመለሱት የኢትዮጵያ ዜጎች የግል ደህንነት ከባድ ስጋት ስለማይፈጥር ነው የተቋረጠው ብለዋል ኖኤም። በዩናይትድ ስቴትስ ለመቆየት ሌላ ህጋዊ መሰረት የሌላቸው ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በፈቃደኝነት ከዩናይትድ ስቴትስ ለመውጣት 60 ቀናት ተሰጥቷቸዋል። በፈቃደኝነት ሚወጡ ኢትዮጵውያን ነጻ የአውሮፕላን ትኬትና 1000 ዶላር ጉርሻ ይሰጣቸዋል ብለዋል ዋና ጸሐፊዋ። ከዚህም በተጨማሪም ህጋዊ የኢሚግሬሽን እድሎችንም ያካተተ ነው። ይሁን እንጅ ከየካቲት 13 ቀን 2026 ዓ.ም በኋላ የሀገር ውስጥ ደህንነት መምሪያ የTPS አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያለ ምንም ቅደመ ሁኔታ ማሰር እና ማባረር ከመቻሉም በላይ ወደ አሜሪካ ተመልሰው እንዲገቡ ፈጽሞ እንደማይፈቀድላቸው ከመግለጫው ለመረዳት ተችሏል። https://www.uscis.gov/newsroom/news-releases/dhs-announces-the-termination-of-temporary-protected-status-for-ethiopia
